ኢትዮጵያ ሥመ - ጥር፤ ጀግና ጨዋ የሠራዊት መሪ ነበራት።
ኢትዮጵያ ሥመ - ጥር፤ ጀግና ጨዋ የሠራዊት መሪ ነበራት። "አቤቱ ንጹህ ልብን ፍጠርልኝ።" አሜን። በዘመኔ ያየኋቸው ቆፍጣና፤ ንቁ፤ ትጉህ፤ ዲስፕሊንድ የኢትዮጵያ የሠራዊት መሪወች፤ የሠራዊቱ አባሎች አቋቋማቸው፤ አረማመዳቸው፤ የአነጋገር ዘይቤያቸው #ቁጥብነት ፤ ሥርዓታቸው፤ የአለባበሳቸው ጥራት ፈጽሞ አይረሳኝም። በእኔ የልጅነት - ዘመን፤ በእኔ የወጣትነት - ዘመን፤ በእኔ የሥራ - ዘመን፤ በእኔ የኃላፊነት እና የተጠያቂነት - ዘመን ያዬኋቸው #ቆፍጣና ፤ #ጥንቁቅ ፤ ኢትዮጵያን እና ኢትዮጵያዊነትን ብቻ #መለዮቸው ያደረጉ ድንቆች አይረሱኝም። ኢትዮጵያ ብቃት ያለው ሠራዊት ነበራት። ያው የኢትዮጵያ የችግር ምንጭ የፖለቲካ ኢሊቱ የአመራር ጥበብ ማነስ ይሁን ሌላ ብቻ በጣም ብዙ መስዋዕትነትን የከፈሉ ዕንቁ የጦር መኮንኖች፤ የሠራዊቱ አባላቱም ህወሃት ሥልጣን ሲይዝ በተናቸው። ያ በተመክሮ፤ በዕውቀት፤ በብቃት የሠለጠነ ተቋም በአመዛኙ በህወሃት አማተር ሠራዊት ተተካ። በጫካ ዲስፕሊን ነገሩ ሁሉ ተቀመመ። የኢትዮጵያ ሊቃናት ስለምን #አድካሚውን መንገድ እንደሚመርጡ ባይገባኝም፤ የትውልዱ ድካም እና ልፋት ባክኖ መቅረቱ ግን በእጅጉ ያንገበግበኛል። በየቤታችን ወንድሞቻችን ገብረናል በናቅፋ በአፋቤት በርሃ። የሆነ ሆኖ ትልቅ ሰው #አይሞትም ህያው ነው። ክቡርነታቸው ልጆችም ስላላቸውም ተመስገን ነው። እኒህን ታላቅ ሰው ኢትዮጵያ ስታጣ ኢትዮጵያን እግዚአብሄር #ያጽናሽ ማለት ይገባል። በተጨማሪም ለቤተሰብ፤ ለወዳጅ ዘመድንም መጽናናቱን እመኛለሁኝ። ከእኛ የቀደመው ትውልድ መራራ ስንብት እያደረገ ነው። አይዋ አይለዬ #ሞት ወደ እኛም እየገሰገሰ ነው። ...