ልጥፎች

አፍንጫህን ላስ – አቶ ሂደት።

ምስል
አፍንጫህን ላስ – አቶ ሂደት። ከሥርጉተ ሥላሴ  ( Sergute © Sselassie ) March 21, 2014 ከጭምቷ ሲዊዘርላንድ። „አቤቱ እንደ ቸርነትህም መጠን ማረኝ፤ እንደ ምህረትህም ብዛት መተላለፌን ደምስስ።“ (መዝሙር ፶ ቁጥር ፩) እኔ ነኝ አቶ ሂደትን አፍንጫውን እንዲልስ የፈለኩት። ሃሳቤን የሚጋራ ትብብር ካለም ደስታውን አልችለውም። በ 16.03.2014 ጀንበር ዘቅዘቅ ከመለቷ በፊት ዘሀበሻ ስገባ አንድ አዲስ መረጃ አገኘሁ። የአንድነትና የመኢአድ ቅድም ውህደት መሰናዶ። http://www.zehabesha.com/amharic/archives/13623 ዘግዬት ብሎ ደግሞ ማምሻ ላይ ለሁለተኛው ቀን በደብተራ ክፍል አዲሱን ዜና አበሰሩ ለታዳሚው የአንድነቱ አቶ ሃብታሙ አያሌው። እንደ ድሮው ቢሆን እንዴት ? ወዴት ? ለምን ? እያልኩ መንፈሴን አመሰው፤ አውከው ነበር። አሁን ግን አዳማጠኩ አቶ ሂደትን ማዬት ነው ፍሬውን። በቃ ! ጅልነት ቀረ ወላለቀም። ነገም የሰይጣን ጆሮ ይደፈንና ከባዶ ሳጥን ቆጠራ በኋላ አቶ ሂደት ሌላ ትዕይነት ይዞ ከች ቢል አፍንጫህን ላስ በመጣህበት መንገድ ብዬ ቅንጡን አብርሬ ማሳፈር። ሞኙን ይፈልግ … . ይበቃል የተዳቀቅነው። ይልቅ አቶ ሀብታሙ በ 16.03.2014 በነገሩን ሰበር ዜና ላይ የተፈለፈለ ቁምነገር አብሬ አዳመጥኩኝ። ኮረቻ ላይ ቁጢጥ ያለ „ ኢጎ “ አላሰራም ካላ በመጣበት መንገድ ለመሸኘት መወሰኑን። ይህ ማለፊያ ነገር ነው። ግን ላይ ብቻ ነው „ ኢጎ “ ያለውን አቶ ሀብታሙ ? ታችም አለና ታቹም