ፕሬዝዳንት ለማ መገርሳ የህዝባቸው ክብር የደም ሥራቸው ነው።
እንኳን ደህና መጣችሁልኝ ምርመራ፤ ክፍል ስድስት ማጠቃለያ። „እግዚአብሄር ፍርድን በማድረግ የታወቀ ነው።“ መዝሙር ፱ ቁጥር፲፮ ፕሬዝዳንት ለማ መገርሳ የህዝባቸው ክብር የደም ሥራቸው ነው። ከሥርጉተ©ሥላሴ Sergute©Selassie 05.04.2019 ከእመ ዝምታ ሲዊዘርላንድ። ውዶቼ እንዴት ናችሁ እንዴት ናችሁ? ደህና ናችሁ ወይ? ባለፈው ክፍል አምስትን በዚህ ነበር የከወንኩት … ይልቅ ሃዘን እጠብቃለሁኝ የአማራ አክቲቢስቶች፤ የአማራ ጦማርያን፤ የአማራ የሚዲያ ሰዎች፤ የአማራ ጋዜጠኞች አዲስ አባባ ላይ ምን እና ምን ይሆኑ ይሆን እንዲህ በቀል በሳንጃ አንቱ ሲሆን እላለሁኝ። እፈራለሁኝ። ማህዲሱ አይማረኛ ላልምርህ ከቤተ መንግሥት መንፈሴ የወጣ ዕለት ስላለ … ስጋቴ ከባድ ነው። ጠረኑን እያፈነፈነ አደነው ነው። አብዝቶ ማድመጥ፤ አላምጦ መዋጥ ለዚህ ዳጥ እና ምጥ ዘመን ማስተዋል ቢሰጠን እላለሁኝ። ዛሬ አይታዬነም ምን አልባት መኖሩ ከተገኜ የዛሬ 10 /15 ዓመት ነው ይህ ውጥን በቅሎ፤ ነፍስ ዘርቶ ነባሩን ሁሉ ደርምሶ ወይኔን የሚያስተቃቅፈው። ቅንነት ጸጋ ነው። ግን ቅንነት ፈተና ሲገጥመው አደብ ገዝቶ መመርምር ይጋባል እንደ እኔ ሰለ ኦህዴድ ስለ ፕ/ ለማ መገረሳ፤ ለመሆኑ ስለ ዶር አብይ አህመድ የሞገት ነበርን? ወደ 300 የሚሆን ጹሑፍ እኮ ነው የጻፍኩት። ይህ ብሎግ በ2014 ነው ዝም ብዬ ሥሙን ሰጥቼ ያሰቀመጥኩት ነበር፤ ሥራውን የጀመርኩት ለአብይ አክቲቢዝም ነበር። ግን ገንግኖ ብዕሬንም ብራናዬንም ሞገተ...