ልጥፎች

ከጃንዋሪ 20, 2025 ልጥፎች በማሳየት ላይ

#ሰላምን የሚገልጽ #ቃል #አልተፈጠረም።

ምስል
  #ሰላምን የሚገልጽ #ቃል #አልተፈጠረም ።      በዚህ አፍላ የሽግግር ጊዜ #የጋዛ እና #የእስራኤል #ተኩስ #አቁም ፣ #የእስረኛ እና #የታገቱ መከረኞች #ንጹህ #አየር #መተንፈስ እጅግ #ተስፋ #ሰጪ ጅምር ነው።    #ተመስገን ። መጨረሻውን ያሳምረው። #የጦርነት #መጨረሻም ፈጣሪ አምላክ፤ አላህ ያድርገው። አሜን።   «የሰው ልጅ መንገድ ያዘጋጃል፤ እግዚአብሄር ግን መንገዱን ያዘጋጃል።»   (ምሳሌ ፲፮ ቁጥር ፱) Sergute©Selassie 20.01.2025 ጊዜ ራዲዮሎጂ ነው።

መልካም #የእረፍት ጊዜ። አሜን።

ምስል
  መልካም #የእረፍት ጊዜ። አሜን።    «የሰው ልጅ መንገድ ያዘጋጃል፤ እግዚአብሄር ግን መንገዱን ያዘጋጃል።» (ምሳሌ ፲፮ ቁጥር ፱)     ለተከበሩት የአሜሪካ ፕሬዚዳንት ለነበሩት ለክቡር ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን እና ለቲማቸው #መልካሙን ሁሉ ይገጥማቸው ዘንድ እመኛለሁኝ። የአሜሪካ መንፈስ #ከግሎባል ዜጎች ጋር በአመዛኙ #የተሳሰረ ነው። ነገረ አሜሪካ #አያገባኝም ማለት የሚቻል አይመስለኝም።    #የሰብዕዊ #መብት #ረገጣ ፥ ወይንም #የሚዛን #መዛባት ሲገጥም #ሲከፋን #አቤት የምንለው ወደ እነሱ ነው። #ታላቅ #ታናሽ ሳይለዩ #በራቸው #ለሁላችንም #እኩል ክፍት ነው። ቲማቸውም #የከበሩ የሰውን ልጅን #የሚያከብሩ ነበሩ። #ያደምጣሉም ። ይህ መቼም #መሰጠት ፤ #መቀባትም ነው። እግዚአብሄር ጨምሮ #ይባርካቸው ። አሜን። #እግዚአብሄር #ይስጥልኝ ። #አመሰግናችኋለሁም ። #ብዕሬ #ሳትደመጥ ቀርታ #አታውቅም እና!    Sergute©Selassie 20.01.2025 ጊዜ ራዲዮሎጂ ነው።

ከአሜሪካ #ፈርስት በሚደንቅ ሁኔታ እግዚአብሄር #ይቅደም!

ምስል
  #የምዕት #ዕንቁ መሪ ፍፁም #ቅዱስ #ቃል ። #የፀደቀም ተነበበ።        ከአሜሪካ #ፈርስት በሚደንቅ ሁኔታ እግዚአብሄር #ይቅደም ! " #አሜሪካን ዳግም #ታላቅ ለማድረግ፦ በአሜሪካ #ህይወት ውስጥ፦ መልሰን የምናስገባው #ታላቁ ነገር፤ #እግዚአብሄር ነው።" (አዲሱ የአሜሪካ ፕሬዚዳንት ክቡር ዶናል ትራንፕ።)     ቃለ ሕይወት ያሰማልኝ። ይህ #የምዕት መሪ ቃል ፍፁም ቅዱስ፤ #የፀደቀም ቃለ ህይወት ነው - ለእኔ። የተባረከ የመሪነት መርህም፤ ቀናም ጎዳና ነው። ቃሉ ኪዳኑ ከፈጣሪ ጋር ነውና አቅሙን የአለም ንጉሥ ክርስቶስ ይስጥ። አሜን።   ለክቡርነታቸው ይህን ዕውን የሚያደርጉበት የህይወት ዘመን ይስጣቸው። አሜን። ይህ መሪ ቃል ከሞት በተደጋጋሚ ያተረፈ፤ ፈቅዶ እና ወዶ ለመረጠ ለቀባ ተደጋጋሚ የዕድል በር ለሰጠ አምላክ የቀረበ #የምስጋና #ስጦታ ነው። የመፈፀም አቅሙን፦ ክህሎቱን መዳህኒዓለም ይሰጥወት ዘንድ እንደ አንድ የግሎባሉ #ባተሌ ዜጋ በፍፁም ልቤ እመኛለሁ። ከቂም፤ ከበቀል የፀዳ መንፈሰ ደርጅቶ፦ መስመሩን አጥርቶ ፈጣሪ ይመራወትም ዘንድ እመኛለሁኝ።   ለእኔ እንደ ቃለ ምህዳን ነው ያዬሁት። ፍፃሜውን ያሳምረው ፈጣሪ። አሜን። በአንድም በሌላ የአለም አገሮች ሆኑ ዜጎች ከአሜሪካ ጋር ትስስር አላቸው እና። ስጋት፤ ጭንቀት፤ ፍርሃት የሰውን ልጅ በቁሙ ይፈትነዋል። በዚህ የአመራር ሽግግር ደስ ያላቸው እንደአሉ ሁሉ የፈሩም፦ የሰጉም ዜጎችም አገሮችም ይኖራሉና።   መሪነት #አጽናኝነት እንዲሆን ፈጣሪ ይርዳ። መሪነት #አረጋጊነት ይሆን ዘንድም አማኑኤል ይርዳ። አሜን። መሪነት ሰባዕዊነት እና ተፈጥሯዊነቴ ይሆን ዘንድ ከሞት ያተረፈ አምላክ ይ...

ከፈጣሪ አምላክ ጋር #እርቀ #ሰላም ማውረድ ለሁሉም ይበጃል። #ለፋኖይዝምም ሆነ #ለአብይዝምም።

ምስል
  ከፈጣሪ አምላክ ጋር #እርቀ #ሰላም ማውረድ ለሁሉም ይበጃል። #ለፋኖይዝምም ሆነ #ለአብይዝምም ።   "የቤትህ ቅናት በላኝ።"   እንዴት ሰነበታችሁልኝ ማህበረ ክብር። እኔ አምላኬ ክብሩ ይስፋ ደህና ነኝ። ዘመነ ብርሃነ ልደት፤ ዘመነ አስተርዬ በአማራ ክልል በትላልቅ ከተሞች በሰላም መጠናቀቁን ሰማሁኝ። የአፍሪካ፤ የአለም፤ የኢትዮጵያም ርዕሰ መዲና በሆነችውበአዲስዬሜ እንዲሁ። በውነቱ ደስም ብሎኛል።    በኦሮምያ ክልል ክልትምትም የሚለው የኢትዮጵያ ኦርቶ ዶክስ ተዋህዶ ሃይማኖት ዓውደ ዓመታት አሁን ከሆነ በአማራ ክልልም መፈጠሩ፦ #መስተጓጎሉ በብዙ አዝንበት የነበረ በኽረ ጉዳይ ነበር። ሰሞናቱ ተመስገን ነው።   እርግጥ ነው በፈታ ደይሊ ዜና እንዳዳመጥኩት አልፎ አልፎ #ጠሽ #ጧ እንደነበር አዳምጫለሁኝ። የሆነ ሆኖ ግን በመላ የአማራ ክልል እና በሌሎችም ክልሎች እግዚአብሄርን ያስከፋ መስተጓጎል ባለመድረሱ ተመስገን ነው።   ጎንደር #የሎዛ #ማርያም ቀጣይ ክብረ በዓል በ21 አለና ከበዓለ እመቤታችን በዓላት ጋርም ግብ ግብ እንዳይኖር፦ በአጽህኖት ለሚመለከታቸው #ለፋኖይዝም አለቆች እና #ለአብይዝም የመንግሥት ሠራዊት አባላት አሳስባለሁኝ።    ከፈጣሪ ፈቃድ ጋር ግብግብ ትርፋ መትነን ነው። ለማንም አይጠቅም። በውነቱ #መባረክን ፤ #መቀደስን ፤ #መመረቅን መፃረር የጤና አይመስለኝም። የሆነ ሆኖ በ ዕዓላቱ በአንፃራዊ ሰላም መጠናቀቃቸው፤ መልካም ነገር ነው። ደንግጬ ነበር በጦር ድሮን #ጥበቃ ይደረጋል፤ #እርምጃም ይወሰዳል ሲባል። ሦስቱም አካላት #ፋኖይዝም ፤ #አብይዝም ፤ #ሽመልዚም ትእግስቱን ሰጥቷቸው በዕላቱ ካለ ህውከት መጠናቀቃቸው መልካም ነው። የፈጣሪ አም...