ልጥፎች

ከፌብሩዋሪ 9, 2026 ልጥፎች በማሳየት ላይ

#በአገራቸው ፓርላማ #ስደት ላይ የነበሩት የህዝብ ተመራጭ እንደራሴ ዶር ደስአለኝ ጫኔ #በቃኝ! አሉ።

ምስል
  #በአገራቸው ፓርላማ #ስደት ላይ የነበሩት የህዝብ ተመራጭ እንደራሴ ዶር ደስአለኝ ጫኔ #በቃኝ ! አሉ።   "አቤቱ የቤትህ ቅናት በላኝ።"   #ምዕራፍ ፲፰።   የዜግነት እርቦ፤ የዜግነት ሲሶ፤ የዜግነት እኩሌታ ያዬሁበት የፓርላማ ጊዜ ነበር ዶር ደሳለኝ ጫኔ እና አራት ጓዶቻቸው በህዝብ ሙሉ ድምጽ ተመርጠው አህዱን …… ክለቱን……… ሰለስቱ……… አርባዕቱ ………፭ኛው ዓመት እንሆ በጣት የሚቆጠሩ ወራት ቀሩ።   ለኢትዮጵያ ፓርላማ #የመተንፈሻ #ቧንቧ የነበሩት የህዝብ እንደራሴው ዶር ደስአለኝ ጫኔ #በቃኝ ! ሲያንስ ነው ባይ ነኝ። ለምን? ያን ሁሉ ግልምጫ፤ ያን ሁሉ ስላቅ፤ ያን ሁሉ መዘባበቻነት፤ ያን ሁሉ ግልምጫ፤ ያን ሁሉ መታፈን፤ ያን ሁሉ የሰው ክቡሩነት የተናቀበት ሂደት ተሸክመው እዚህ መድረሳቸው የሚገርመኝ፤ የሚደንቀኝ ገጠመኝ ነበር።   እኔ በተፈጥሮዬ መጀመሪያ የማዬው #ገጽን ነው። ገጹ የተከፋ የማንኛውም ሰብዕ ሁነት ከተመለከትኩ፤ ከዛች ቅጽበት ጀምሮ #ወራጅ አለ ነው።   #እንዲህም ሆነላችሁ።    በአንድ ወቅት ህዝባዊ ስብሰባ በርን ነበር። ከቪንተርቱር በርን በራሴ ወጪ ተጓጉዤ ሄድኩኝ። የጋበዙኝ ሰወች፤ ለማደሪያም ቦታ እንደተዘጋጀልኝ ተነግሮኝ ነበር የሄድኩት። ቃል የገቡት ግን አልተገኙም። እኔ ግን ቀድሜ ተገኜሁኝ። የተፈለግሁበት መሠረታዊ ምክንያት #አሽሙር እንዳደምጥ ነበር። እኔ ሥርጉተሥላሴ የየትኛውም የፖለቲካ ድርጅት ቁሮ እንጨት ወይንም ልጥፍ ከሰል ለመሆን መቼውንም አልፈቅድም። የራሴ እንደራሴ እራሴው ነኝ።    እናላችሁማ #ቆፍጣናዋ ጎንደሬ የሄደችው " #የፈራ ይመለስ" 500 ወጣቶች ቲሸርት በራሳቸው ወጪ አሰርተው የበዓቴ አንበሶች ህ...

ዛሬ ችሎት ከቀረቡት ተከሳሾች መካከል ሰባቱ በነጻ እንዲሠናበቱ ችሎቱ መወሰኑን

  Daniel Bekele   · በእነ ጋዜጠኛ መስከረም አበራ የክስ መዝገብ በሽብር ወንጀል የተከሰሱ 16 ተከሳሾች ክሳቸውን እንዲከላከሉ ብይን ተሠጠ። የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ ችሎት 1ኛ ጸረ-ሽብር ወንጀል ችሎት፣ በጋዜጠኛ መስከረም አበራ፣ ገነት እስማማው፣ ጎበዜ ሲሳይ እና ዳዊት በጋሻው የክስ መዝገብ በቀረበው የአስተያየት ሰነድ ላይ "ክሱን ይከላከሉ ወይም አይከላከሉ" በሚለው ጉዳይ ላይ ብይን ለመስጠት ለዛሬ ጥር 28 ቀጠሮ ሠጥቶ እንደነበር ይታወሳል።    ችሎቱ፣ በእነ ዶ/ር ሲሳይ አውግቸው መዝገብ ሥር የተካተቱ ተከሳሾች የዋስትና ክርክር እንዲያደርጉ ብይን በመስጠት ለሚያዚያ 23 2018 ዓ፣ም ተለዋጭ ቀጠሮ ሠጥቷል።    ዛሬ ችሎት ከቀረቡት ተከሳሾች መካከል ሰባቱ በነጻ እንዲሠናበቱ ችሎቱ መወሰኑን ዋዜማ ከተከሳሾቹ ጠበቆች ሠምታለች። በዛሬው ችሎት በጠቅላላው በክስ መዝገቡ ከተካተቱት 51 ተከሳሾች መካከል ችሎት የቀረቡት 23ቱ ናቸው።   ዋዜማ ራዲዮ February 5, 2026 ፎቶው የቆየ ነው።

#የጠይም #ዕንቁ የእልልታ ዜና። "ኢትዮጵያዊው ሳይንቲስት በተመድ መንበር ላይ ተሰይሟል"

ምስል
    #እሰይ #እልል ። እስኪ ቸር ዜና ይዛችሁ ከች በሉልን።       "አድርገህልኛል እና አመሰግንሃለሁኝ።" አንድ ቀን፣ አወን አንድ ቀን ኢትዮጵያ #ተመድን የመምራት ዕድል ይኖራታል። ከጥቁር አልማዝ ይልቅ ጠይም ዕንቁ ቢባሉ።    ከአቶ Trotsky Wendesse የተገኜ የምስራች ነው። አድካሚ ቀን ነበረኝ ዛሬ ግን ይህን መሰል ዜና ብርታትን ይቸራል። "አድርገህልኛል እና አመሰግንኃለሁኝ።"    መልካም የሥኬት የምርምር ዘመን ይሆንላቸው ዘንድ እመኛለሁኝ። ኢትዮጵያም እንኳን ደስ አላት።    ========== "ኢትዮጵያዊው ሳይንቲስት በተመድ መንበር ላይ ተሰይሟል ከኒውክሌር ጦር መሳሪያ በላይ ዓለምን እያስፈራት ያለው የሰው ሰራሽ አስተውሎት (AI) ጉዳይ፣ ዛሬ በአንድ ስመ-ጥር ኢትዮጵያዊ ሳይንቲስት እጅ ላይ ወድቋል። ይህ ወጣት አዕምሮ፣ ከሀርቫርድ እስከ ኦክስፎርድ፣ ከማይክሮሶፍት እስከ IBM የጥበብ ማማዎች ላይ ተራምዶ፣ ዛሬ በተባበሩት መንግስታት ድርጅት (UN) መንበር ላይ ተሰይሟል! የሳይንሱ ኮከብ ጉዞ • የማይክሮሶፍት ኩራት፦ በ "AI for Good" ላቦራቶሪ ውስጥ ዓለምን የሚለውጡ ምርምሮችን ሲመራ ቆይቷል። • የኦክስፎርድና ሀርቫርድ አሻራ፦ ማሽኖች ለሰው ልጅ ጤና እንዴት እንደሚሠሩ በሚያስደምም ጥልቀት የመረመረ ባለሙያ። • የዕውቀት ጎተራ፦ ከ27 በላይ ዓለም አቀፍ የሳይንስ ምርምሮችን ለዓለም ያበረከተ የዘመኑ ጥቁር አልማዝ። የተመድ ዋና ጸሐፊ አንቶኒዮ ጉተሬዝ በአውሮፓውያኑ ጥር 26 ቀን 2018 ዓ.ም. ባስተላለፉት ታሪካዊ ውሳኔ፣ ዶ/ር ግርማው ከዓለም ዙሪያ የተውጣጡ 40 ታዋቂ ምሁራንን እንዲመራና እንዲያስተባብር በይፋ ሾመውታል። "ኢትዮጵያ በዲጂታ...

#ጉግት ለጦርነት ጠቃሚ አይደለም። ሞት #ጎትትም ነው። ቂምና #በቀል የሚያዘምርም ነው።

  #ጉግት ለጦርነት ጠቃሚ አይደለም። ሞት #ጎትትም ነው። ቂምና #በቀል የሚያዘምርም ነው።    "አቤቱ የቤትህ ቅናት በላኝ።"   ጤናይስጥልኝ አዱኛወቼ የብዕሬ እና የንጹህ መንፈሴ ፈቃደኛ አድማጮቼ እንዴት አላችሁልኝ?   ጦርነት #ብራቮ ጎሽ የምትሉት ሰው ሰራሽ አውዳሚ ክስተት ሊሆን የሚችል አይደለም። ጦርነት ተገደውም ይሁን ፈቅደው ይጀምሩት ለድል የሚያበቃ፤ ለትውልድ #ቅርስ ውርስ የሚሆን ጉዳይ አይደለም። የአለማችን ፖለቲከኞች ጦርነትን #በሁለት ይከፍሉታል። #ህጋዊ (አመክኖያዊ ወይንም ምክንያታዊ) እና #ህገወጥ (አልቦሽ ምክንያታዊነት) ብለው። ህጋዊም ይሁን ህገወጥ ማገዶው የሰው ልጅ ነው። እንጨት እንጂ የሰው ልጅ የተፈጠረው ለማገዶ አይደለም።   ፈጣሪ የረዳው #እንጨት ለታቦትም ይሆንና አክብሮተ ነገሩ ሰማያዊ ይሆናል። የሆነ ሆን ጦርነት እቅዱ ምንድን ነው ከተባለ #የእናቶችን #መሃጸን #ለቄራነት ማሰናዳት ነው። በዚህ በያዝነው ወር የዘለንስኪዝም ዕቅድ በወር 50ሺህ የራሺያ እናቶችን ማህጸን ወደ " #ሊኳንዳ " ቤት መውሰድ ነው። ለቃሉ ይቅርታ እጠይቃለሁኝ።    ይህን የሚያወግዝ ሰላማዊ ሰልፍ ዓለማችን አላሰናዳችም። እጅግ ያሳዝናል። ጦርነቱ እንደተጀመረ ዘለንስኪዝም እስከ 10 ዓመታት የመዋጋት አቅም አለን ብለው ነበር። ይህም የዩክሬንን እናቶች ማህጸን በታቀደ #ቄራነት ያሰላ ነበር። ይህን ጨካኝ እይታ ዓለማችን ከማውገዝ ተቆጥባ #እንክህ እንክህ ስትል ስመለከት ማህጸኔ እንደ ዱባ ይቀረደዳል።   የእስከዛሬው አልበቃ ብሎ የኤርትራ መንግሥት እና የኢትዮጵያ መንግሥት በባህር በር የይገባኛል ምክንያት ጉጉሡ ተጠናክሮ ቀጥሏል። ተካሯልም። #አይጠቅምም ። በፍጹም አይ...