ልጥፎች

ከጁላይ 24, 2024 ልጥፎች በማሳየት ላይ

መሪነት መፍትሄ አመንጭነት ነው።

 መሪነት መፍትሄ አመንጭነት ነው። #አጤ #ሽዋስ እንዴት አደረ ይሆን? ዬአጣዬ መከራ ከውስጡ ያልገባ የአመራር ሂደት ያ ሁሉ መከራ አልበቃውም፦ የአጣዬ የሽዋ ሮቢት ያ ሁሉ ስቃይ ተዘሎ አሁን ደግሞ እንደ ዳንቴል #በእጅ #በተሠራ #መከራ #አሳሩን እያዬ ነው።  አዝናለሁ ሕዝባችን እንዲህ ከመከራ ላይ መከራ ተሸከም ተብሎ ፍዳውን ማዬቱ። ደብረብርኃን መጠለያ ያሉት ወገኖቻችን ስቃይ እራሱ #ሐዋርያ በሆነ ነበር።  መጠለያ ላሉትም #ተስፋቸውን ሙልጭ አድርጎ #የዘረፈ // #ስጋትን #አጭቶ ያነገሠ ጉግስ ነው እያዬሁት ያለሁት። ልብ ይስጣቸው ለመሪወቹ። አሜን። "የቤትህ ቅናት በላኝ።"  ሥርጉትሻ 2024/07/24

#ቅኔው ጎጃም ላይ ያዬሁትም ዕውነት ከሆነ እጅግ አሳዝኖኛል።

  #ቅኔው ጎጃም ላይ ያዬሁትም ዕውነት ከሆነ እጅግ አሳዝኖኛል። ቢያንስ ለአማራ እናት #ዕንባ መቆም እንዴት ይሳናል? ባልተለመደ ሁኔታ #በእናቶች ላይ የሚፈፀመው፤ በግራጫማ ፀጉር ባበቀሉ ወገኖች ላይ ያዬሁት የእንብርክክ ስቃይ፤ የከፋም እርምጃም ሰማሁ ለዚህ ነው ሙሉ ቅኔው ጎጃም ከሐምሌ 5 ጀምሮ መኖሩን የሰጠው? ለዚህ ነው? ለጭካኔ? ከጨካኝ ተሽሎ መገኜት እንዴት አይቻልም? ሙሉ የጦርነቱ አቅም የፈሰሰው እኮ ቅኔው ጎጃም ላይ ነው።  የጠቅላይ ሚር አብይ አህመድ አገዛዝ የውጭ አገር ቅኝ ገዢ እስኪመስለኝ ድረስ #በእልህ ማቱን ያፈሰሰው በዚህ ጨዋ ህዝብ ላይ ነው። ከመጀመሪያዋ ከሐምሌ 5ቱ የተጋድሎ ንቅናቄ ጀምሮ #በጠና አቅም እና #አቋም ሳይሽረከረክ፦ ለመደለያ ሳያድር የትግሉን መንፈስ ያስቀጠለ ጀግና ህዝብ እንዴት በተስፋወቹ ይቀጣ? ግፍ አይሆንም? አልቅሻለሁ። የት ይሂድ ይህ ህዝብ? ምርጫ አለውን? ማስተማር መንገር ማሳመን እያለ እንደዛ? ነገስ??? ሥርጉ2024/07/24

ጎፋን ለምትደግፋ ጥሩወች።

ምስል