ልጥፎች

ከማርች 27, 2021 ልጥፎች በማሳየት ላይ

ልጆአቻችን መልሱልን።

ምስል
  እንኳን ወደ ከበቡሽ ብሎግ በሳላም መጡልኝ።   በከበቡሽ የቁራሽ እንጀራ ብራና በቢሆነኝ የተብራራ ብራ በሰብለ ህይወት አዝመራ ለራህብ የሚራራ። „የሰው ልብ መንገድን ያዘጋጃል እግዚአብሔር ግን አካሄዱን ያቃናለታል። (ምሳሌ 16 ቁጥር 9) ·       አደ ናግሬው ጠቅላይ ሚኒስተር መቼ ይሆን ከዕውነት ጋር የሚገናኙት? ·       መ ቼ ነው የሚያልቀው ይሆን የአጤ ዝናቡ የጠቅላዩ የኢትዮጵያዊነት ዲስኩር? ·       መ ቼ ይጠናቀቅ ይሆን ይህን ዕብለትን ተሸክሞ ማምታቱም? „ስለ ሉዓላዊነቴ አንገቴ ይቀነጠሳል“   ይላሉ? ወይ አፍረት አለመኖር። ይህ አንድ ሽፋታ የፈጸመው ድፈረት ሉዕላዊነት አለመደፈር ይሆን? ለመማር የሄዱ ልጆች እንዲህ ድበዛቸው ጥፍት ሲል መሪ ነኝ ብሎ ለማናገር በዬትኛው ሞራል? በዬትኛው የማስተዳደር፤ የመምራት፤ የማቀናጀት አቅም? አብረው ፈጽመወት ካለሆነ በስተቀር መቼም ይህ ክብር ሆኖ የኢትዮጵያ መሪ፤ የጦር ኃይሎች ጠቅላይ አዛዥ አያስብልም። ፈጽሞ። ማፈሪያ!   እግዚአብሄር ይስጥልኝ። አሜን። ሥርጉተ©ሥላሴ Sergute©Selassie 27.03.2021 ጎዳናዬ ሰብዕዊነት ነው!

መቼ ነው የእናንተን ሳቅ እኔ እማዬው?

ምስል
  እንኳን ወደ ከበቡሽ ብሎግ በሳላም መጡልኝ።   ዕለተ ሰንበት ማዕዶተ ርትህ ሰባዕዊነት በከበቡሽ የቁራሽ እንጀራ ብራና በቢሆነኝ የተብራራ ብራ በሰብለ ህይወት አዝመራ ለራህብ የሚራራ። „የሰው ልብ መንገድን ያዘጋጃል እግዚአብሔር ግን አካሄዱን ያቃናለታል። (ምሳሌ 16 ቁጥር 9) ·        መ ቼ ነው የእናንተን ሳቅ እኔ እማዬው? መቼ ይሆን ወደ ሰላማዊ ህይወት ተመልሳችሁ ለከፈላችሁት መስዋዕትነት ሁሉ ምስጋና ወግ ደርሶን እምናቀርብላችሁ? መቼ ነው   የእናንተ ስቃይ ተሰምቶን የተደራጄ ማህበራዊ ንቅናቄ አድርገን ከካቴና እምናላቅቅላችሁ? እናንተን ሳይ አፍራለሁኝ። እማፍረው በራሴ አቅም ነው። እንዲህ ዕድሜ ዘመናችሁን ሁሉ ኢትዮጵያን ብላችሁ ክልትምትም? ወጣትነታችሁ ተጠናቀቀ? ጎልመሳናችሁም እንዲሁ? አዝናለሁኝ። እናንተን ሳስብ ማህጸኔ እንደ ዱባ ይቀረደዳል። አቅመ ቢስነት ይሰማኛል። በተለይ አሁን የገደበን አቤቱ ኮሮናም ጭምር ነው። እሱ ክፉኛ ፈተነን። የእኔ ጀግኖች አይዟችሁ። እግዚአብሄር ይስጥልኝ። አሜን። ሥርጉተ©ሥላሴ Sergute©Selassie 27.03.2021 ጎዳናዬ ሰብዕዊነት ነው!

ይድረስ ለዶር ዳንኤል በቀለ

ምስል
  እንኳን ወደ ከበቡሽ ብሎግ በሳላም መጡልኝ።   ዕለተ ሰንበት ማዕዶተ ርትህ ሰባዕዊነት በከበቡሽ የቁራሽ እንጀራ ብራና በቢሆነኝ የተብራራ ብራ በሰብለ ህይወት አዝመራ ለራህብ የሚራራ። „የሰው ልብ መንገድን ያዘጋጃል እግዚአብሔር ግን አካሄዱን ያቃናለታል። (ምሳሌ 16 ቁጥር 9) ማዕዶተ ርትህ ሰባዓዊነት። ይድረስ ለዶር ዳንኤል በቀለ የሰባዕዊ መብት ኮሚሽን ኮሚሽነር አዲስ አበባ። የማክበረዎት ዶር ዳንኤል ሆይ! አንድ ጊዜም ይህን ጉዳይ አጽህኖት ሰጥቼ አንስቼ ነበር። አዲስ አበቤ ሰብዕዊ መብቱ ሲረገጥ ባለቤት የለውም። ምንም የመኖር ዋስትና የለውም። ልጆቹ በዬዘመኑ በ አደባባይ ይረሻናሉ፤ ካሳ ተከፍሎት እንኳን አያውቅም። ልጆቹ በሰማዕትነት ተዘክረው አያውቁም። እኔ ይህ ለምን ሆነ ብዬ ሳስበው፤ ሳወጣ ሳወርደው አዲስ አበባ ላይ ራሱን የቻለ አንድ የሰብዕዊ መብት ኮሚሽን ግብረ ኃይል እንደሚያስፈልግ ይሰማኛል። በሚመጣው ምርጫም ብዙ ቀውስ ሊከሰት ይችላል። ከ አሁኑ ችግሩን ኮሚሽነዎት ተረድቶ ከማንም ከምንም ከዬትኛውም ክልል ያልተዳበለ የ አዲስ አበቤ የሰባዕዊ መብት ኮሚሽን ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ይከፍቱ ዘንድ በታላቅ ትህትና አክብሮት እጠይቃለሁኝ። አስፈሪ ደማና፤ አስፈሪ ድባባ ነው ያለው። ከምርጫ ጋር ተያይዞ በጣም እጅግ በጣም ተጎጂ የሚሆነው አዲስ አበቤ ነው። የሚያሳዝነው ጉዳቱ እንኳን በ አግባቡ አይዘገብም። የተጎጂ ቤተሰቦች ሥማቸውን እንኳን አናውቅም። ከሰኔ 16/2010 ጀምሮ እስከ ሸኜነው ሳምንት ድረስ አዲስ አበባም የደም ከተማ ሆና ነው የባጀችው። ሟቾቹ ደመ ከልብ ናቸው። ሰፊ የቃጠሎ፤ የዝርፊያም መከራ ሊኖር ይችላል። የትንንቅ ጊዜ ነውና። እባክዎት አቤቱታዬን ከጉዳይ ጥፈው አንድ መላ...

ሰባዕዊነት ለአጤ ዝናቡ ለዶር አብይ አህመድ አልተፈጠረም። ጸጋቸውም አይደለም።

ምስል
      እንኳን ወደ ከበቡሽ ብሎግ በሳላም መጡልኝ።   ዕለተ ሰንበት ማዕዶተ ርትህ ሰባዕዊነት በከበቡሽ የቁራሽ እንጀራ ብራና በቢሆነኝ የተብራራ ብራ በሰብለ ህይወት አዝመራ ለራህብ የሚራራ። „የሰው ልብ መንገድን ያዘጋጃል እግዚአብሔር ግን አካሄዱን ያቃናለታል። (ምሳሌ 16 ቁጥር 9)   ·        ሰ ባዕዊነት ለአጤ ዝናቡ ለዶር አብይ አህመድ አልተፈጠረም። ጸጋቸውም አይደለም። ·        ማዕዶተ ሰባዕዊነት ለዛውም በሰንበት። በኦሮሙማ ጭካኔ ውስጥ ርህርህና ጠብ ይላል ብሎ ማሰብ ከጅልነት በላይ ነው። የተፈጠረው ለጭካኔ ነው። ደም አፍሶ ለመርካት፤ አፍርሶ ለመርካት። አውድሞ ለመርካት። ገድሎ ለመርካት። አስሮ አሰቃይቶ ቤተሰብ በትኖ ለመርካት። ይህ ሁሉ ምድር የማትችለው የሰባዕዊ መብት ረገጣን ኦፕሬሽን በበላይነት የሚመሩት አጤ ዝናቡ ዶር አብይ አህመድ አንዲት ጠጠር የጠፋባቸው አይመስሉም። ጌታዋን የገደለች በቅሎ መስለው ማይካቸውን ቴራፒ እያደረጉ ሰለ ሰው ልጅ እኩልነት፤ ስለዜግነት፤ ስለሰፈርትኝነት ጠያፍነት ይሰብካሉ፤ ይናገራሉ ይደሰኩራሉ። ምን አበቀላቸው? ስለምንስ ተፈጠሩ? ፈታሪ ምን አስከፍተነው ይሆን እንደዚህ ያለ አሳቻ ሰብዕና ይፍጃችሁ ብሎ የፈጠረብን። በእውነት ተረግመናል። እንጹም፤ እንጸልይ፤ እንስገድ፤ እንውደቅ። ፈጣሪያችን ይቅርታ እንጠይቅ። ሰባዕዊኒት እንዲህ በሚነድባት አገር መኖርን ማሰብ እንደምን ይቻል? እነኝህም የ እኛ ናቸው። ልንጮህላቸው ይገባል። ጩኽታችን ለላይኛው ጌታ ለአምላካችን ለፈጣሪ ለአላህ ነው።   አቤቱታችን ለ አንድዬ ነው። ...

መከረኛው አቶ እስክንድር ነጋ እና ቲሙ ... በአሳቻው ጠቅላዩ ...

ምስል
  እንኳን ወደ ከበቡሽ ብሎግ በሳላም መጡልኝ።   ዕለተ ሰንበት ማዕዶተ ርትህ ሰባዕዊነት በከበቡሽ የቁራሽ እንጀራ ብራና በቢሆነኝ የተብራራ ብራ በሰብለ ህይወት አዝመራ ለራህብ የሚራራ። „የሰው ልብ መንገድን ያዘጋጃል እግዚአብሔር ግን አካሄዱን ያቃናለታል። (ምሳሌ 16 ቁጥር 9) ማዕዶተ ርትህ ሰባዕዊነት። ·         ኢ ትዮጵያን ከፈጠራት ፈጣሪ ጋር ግብግብ የገጠሙት አጤ ዝናቡ እና ሰባዕዊነት። ውዶቼ ሰሞኑን በገጠመኝ የቴክኒክ ችግር ምክንያት የልብ የሚያደርስ ተግባር ላልከውን እችላለሁኝ። የሆነ ሆኖ በጥቂቱም ቢሆን ባለችው ትንሽዬ ቀዳዳ እዬሞካከርኩኝ ነው። ·        ሰ ው መሆን ባልተቻለበት አስተዳደር ሰውነትን ውለድ ለማለት ይከብዳል። መዋዕለ ዕድሜውን፤ መዋዕለ መንፈሱን፤ መዋዕለ ተፈጥሮውን ለእናት አገሩ የሰዋው የአቶ እስክንድር ነጋ ሰብዕና እንዲህ በጭካኔ ሲቀጠቀጥ ይህ ትውልድ ተስፋው በምን ያህል መከራ ውስጥ እንደ ተዘፈቀ ማዬት ይቻላል። ጠቅላይ ሚኒስተር አብይ አህመድ ስንት ዓይነት ሰው እንደሆኑ እያዬሁኝ ነው። ዕዳ ከሜዳ አሰኝቶን ብዙ በጣም ብዙ ስለ እሳቸው ደከምን በተለይ እኔ። ስለሳቸው ፍዳ ታዬ። ስለሳቸው ወገኖቻችን አስከፋን። ይሆኑ መስሎን። ተፈጥራዊነት፤ ሰዋዊነት አብዝቶ ይናገሩት የነበረው ግርዶሽ አታለለን። ዓለማችን የባህሪ መነጠር አልፈለሰመችም እና። እንሆ እሳቸው ታምነው መከራን ጠንስሰን፤ መከራን አዋለድን። አዝናለሁኝ። በጣም። እጅግ በጣም። ሳጃም፤ ቦንቡን፤ መድፉን፤ ስላቁን፤ መሰቃውን ቻልን። መቻል ግድ ነውና። የተረገመው መጋቢት 18/2010 ጉልት ብለን ያደርን...

ልደቱ እና ህማማቱ።

ምስል
  እንኳን ወደ ከበቡሽ ብሎግ በሳላም መጡልኝ።   ዕለተ ሰንበት ማዕዶተ ርትህ ሰባዕዊነት በከበቡሽ የቁራሽ እንጀራ ብራና በቢሆነኝ የተብራራ ብራ በሰብለ ህይወት አዝመራ ለራህብ የሚራራ። „የሰው ልብ መንገድን ያዘጋጃል እግዚአብሔር ግን አካሄዱን ያቃናለታል። (ምሳሌ 16 ቁጥር 9) ·        ማዕዶተ ሰባዕዊነት ለዛውም በሰንበት። እንዴት ናችሁ ቅኖቹ? ደህና ናችሁ ወይ? ·        የሰ ውነት ህማማት። ርህራሄ በተሰደደበት፤ ሰውነት በክፋት በሚጨፈጨፍበት፤ መኖር በበቀል በሚከተከትበት፤ ቂም የመንግሥት መርህ በሆነበት፤ በቀል የምንግሥት „ፍኖተ ብልጽግና“ በሆነበት፤ አገር ላይ ሰባዕዊነት ይመጣል ብሎ ማሰብ ከጅልነትም ከፍ ያለ ነው።   በተደራጀ፤ በተቀነባበረ፤ በሥር ዓት በሚመራ የበቀል ኦፕሬሽን ላይ ስለ ትውልድ፤ ስለ አደራ፤ ስለ አገር፤ ስለመኖር ማሰብ መርግ ነው። ኢትዮጵያን ቁጭ አድርጌ፤ በ አቶ ልደቱ አያሌው የመሠራውን ግፍ ፊት ለፊት አስቀምጬ አሟግታቸዋለሁኝ። ከዛ የትውልዱን ተስፋ ሳስብ መቃብር ይወርድብኛል። ይህ የኦሮሙማ ሥርዓት ሊወገድ ይገባል። ርህርሄ ለ እኛ ከሌለው ለ እንጨቱ፤ ለወንዙ፤ ለሳር ቅጠሉ ለማን ሊሆን ነው። እያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ ሰው ይህን አመክንዮ ፊት ለፊት አቅርቦ ሊያወያዬው ይገባል። ሰው መሆናችን ካልካድነው፤ ተፈጥሮን ካልቀበርነው በስተቀር አንድ ኢትዮጵያዊ ዜጋ ይህን ያህል በደል ሲፈጸምበት ይህ የ ኦነግ አመራር በቃህ ሊባል ይገባዋል። በውነቱ ትዕግስትን የሚፈትን መከራ ነው ኢትዮጵያ ውስጥ ያለው። ይህን ነውር ዓለም በትክክል ቢነ...