ነሐሴ አንድ ቀን ስተራሳት አንተን ገድለኸዋል።
ሰማዕትነት ያፈራው እሸታዊ ማንነት። „እንደዚሁ ሁሉ እግዚአብሄር የዘራቸው ነፍሳት ፈጥነው ይነሣሉ፤ እሱ ሰውን በውነቱ ካለመኖር ወደ መኖር አምጥቶ ፈጥሮታልና፤ በምታድን ቃሉ ፈጥኖ ያስነሣቸዋል፤ ማስነሣቱን አያዘገይም።““ መቃብያ ቀዳሚዊ ምዕራፍ ፲ ቁጥር ፮ ከሥርጉተ©ሥላሴ 07.08.2018 ከገዳማዊቷ ሲዊዘርላንድ ገድለ አማራ በባህርዳር ደም የተገበረበት የአማራ የማንነት ታአገድሎ ዕሴት! አማራ የግፍ ቀንበሩን በበቃኝ ታገድሎውን አህዱ ያለበት የሀምሌ 5ቱ 24ቱ ተጋድሎ ጎጃምን በቅኔያዊ ደሙ አንድ ያደረገበት ዕለት ነው ነሃሴ 1 ቀን። እንሆነ የተጋድሎው የህዝበ ውሳኔ ዕወጃ ሰነድ በደም ማህተም የተዘከረበት የደም ዋጋ ቀን። „እሱ ሰውን በውነቱ ካለመኖር ወደ መኖር አምጥቶ ፈጥሮታልና፤ በምታድን ቃሉ ፈጥኖ ያስነሣቸዋል፤ ማስነሣቱን አያዘገይም።“ የማዳን መለከት ከእዮር የተላከልን ሰሞናት ነበር ከሀምሌ 5 አስከ ነሀሴ አንድ 2008 ድረስ ያለው። ዕሴታዊ የደም ግብር የድንጋጌ ዕለት መስከረም 1 ቀን። ትንግርት በደም ቀልሞ ተጋድሎው ጽናዊታዊ ድልድይ የተዘረጋበት ቀን ነበር ነሃሴ 1 ቀን 2008። ይህ ቀን ለአማራነት ፍጹም ልዩ ቅዱስ ቀኑ ነው። ሰማዕትነት ፈቅደው ሲቀበሉት ግብሩ በቅሎ - ጸድቆ - አስበሎ እንዲገኝ ቃል ኪዳን የሚታደስበት ስለሆነ "የበሉበት ወጪት ሰባሪ ላለመሆን" የተግባር ቋጠሮን በቆረጠ እና በወሰነ አቋም ለማዝለቅ ውል ከእነዚያ 76 ሰማዕታት ጋር ጎሎጎታን የምናስብበት፤ ቃላቸውን ብንበላ፤ ኪዳናቸውን ብናፈርስ በቁማችን እንፈርስ ዘንድ እምንወሰንበት እለት ነው። ሰማዕቱን ማሳብ ብቻ ሳይሆን ዕውን የታገድሎው ዓላማ ገብቶን ከሆን በህይወት ያሉትን ጀግኖቻችን ድም...