ልጥፎች
ከኦክቶበር 31, 2024 ልጥፎች በማሳየት ላይ
ጠቅላይ ሚር አብይ አህመድን "በብልጽግና" መንደር የሆነ ነገር #ቢፈጠር ማን ይተካቸዋል? ለሚለው #ጠቅላዩ መልስ ሰጥተዋል ብዬ አስባለሁኝ።
- አገናኝ አግኝ
- ፌስቡክ
- X
- ኢሜይል
- ሌሎች መተግበሪያዎች
ጠቅላይ ሚር አብይ አህመድን "በብልጽግና" መንደር የሆነ ነገር #ቢፈጠር ማን ይተካቸዋል? ለሚለው #ጠቅላዩ መልስ ሰጥተዋል ብዬ አስባለሁኝ። "የቤትህ ቅናት በላኝ።" የህወሃት ህገ - መንግሥት ተጥሶ ከምል #ተጠቅጥቆ ፦ የፓርላማው ጉባኤ ኃላፊነት እና ተጠያቂነት #ጭብጥብጥ ተደርጎ በራሳቸው ፈቃድ በአናርኪዝም መርኽ ሚኒስተሮቹን ሿሿሙ ---:ጠቅላይ ሚር አብይ አህመድ። ለሚያረገርገው ካቤኒያቸው በዬጊዜው ሲያነሱ፤ ሚኒስተሮቻቸውን ሲያሽቀነጥሩ፤ በዲሞሽን ሲያንበሸብሹ ባሊህ ባይ የላትም ኢትዮጵያ። #ሃግ የሚልም የለም። በስንት ሽልንግ #ጦቢያን ዶር አብይ አህመድ አሊ እንደ ሸመቷት አይታወቅም። እንዲያ ወፍ የቀናው ዕለት በሥርዓተ አልበኝነት ህግ ጥሰው የሹመት ዓዋጁን ያስነኩታል። በሳቸው #የተጨባበጠው ፓርላማም ባሰኛቸው ቀን #ይሁንታ ይሰጥላቸዋል። መታደል ይባል መገደል አላውቅም። ኢንጂነር አንሻን የመከላከያ ሚር አደረጓቸው። ወዲያው በዲሞሽን ከሆነ ቦታ ወስደው ሸጎጧቸው። በዛ ሰሞን ደግሞ ቀኑ ላልታወቀ ጊዜ ተልዕኮው ለምን እንደሆን ባናውቅም ዶር አብርኃም በላይ ተነስተው ኢንጂነር አንሻ የመከላከያ ሚር ሆነው ተሹመው አይተናል። የሚባንን ጉድ። ወደ ቀደመው ጉዳዬ ስመለስ በዚህኛው የሹመት ሂደት እንዲያው በመፈንቅል ይሁን፦ በተፈጥሮ ሁኔታ አንድ ነገር ቢፈጠር ጠቅላይ ሚር አብይ አህመድን ማን በብልጽግና ሠፈር ይተካል ለሚለው የዲፕሎማሲው ማህበረሰብ ስጋት፦ እራሳቸው ጠቅላይ ሚር አብይ አህመድ መልስ ሰጥተዋል። ቀዳማዊ እመቤትነቱም በፍትህ ሚኒስተርነት ቀድመው ቁብ አድርገዋል። የህግ ባለሙያው ዶር ገዲወን ጢሞቲወስ ከዲፕሎማሲው ማህበረሰብ ጋር ይተዋወቁ ዘንድ ሁለተኛ ዕድል ...