ኦ! አብይ እንኳንም የእኛ ሆንክልን!
ለብጹዕን አቨው ይስሃቅን አማኑኤል ሰጣቸው። „ጻድቃን ሆይ በእግዚአብሄር ደስ ይበላችሁ፤ ለቅኖች ምስጋና ይገባል።“ መዝሙረ ዳዊት ምዕራፍ ፴፪ ቁጥር ፩ ከሥርጉተ©ሥላሴ 10.09.2018 ከገዳማዊቷ ሲዊዘርላንድ። ኑሩልን! "በስም አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አህዱ አምላክ፤ አሜን!" ሳይገባኝ እና ሳልመቼው የደጀሰላሙን ታምራት እናገር ዘንድ ተገደድኩኝ። „ያዬነውን እንናገራለን የሰማነው እንመሰክራነን።“ እንዲሉ፡፡ · መነሻዬ። https://www.youtube.com/watch?v=_O_sP971z3k ጠ / ሚ ዶ / ር አብይ አህመድ ለብጹዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆሪዎስ የመኖሪያ ቤት ቁልፍ አስረከቡ ይላል ፋና ቴሌቪዥን ያገኘሁት ዘገባ። ትናንት በጨርፍታ ነበር ዛሬ ዘ...