ይድረስ ለኢትዮጵያ አገራዊ የምክክር ኮሚሽን። ኢትዮጵያ - አዲስ አበባ።
ይድረስ ለኢትዮጵያ አገራዊ የምክክር ኮሚሽን። ኢትዮጵያ - አዲስ አበባ። "እግዚአብሄር በአንድም በሌላም ይናገራል ሰው ግን አያስተውለውም" የኢትዮጵያ አገራዊ የምክክር ኮሚሽን ለማን እና ስለማን ይሆን የተቋቋመው??? #ስለአለቅትነት ይሆን??? አነሳችሁብኝ። እንደምን ሙሁራን ለሚያቀርቡትገንቢዕይታ ዕውቅና መስጠት ተሳናችሁ???? #ቁስለት ! የተከበሩ ፕሮፌሰር ሚንጋ ነጋሽ ከአደባባይ ሚዲያ ጋር ያደረጉትን ቃለ ምልልስ በጥሞና ለአራት ጊዜ ያህል አዳመጥኩት። አምስተኛውም ለአዲሱ ዓመት ተቀጥሯል። አይጠገብም። ተቋም ነው። የአወያዩ የአቶ አቤል ጋሹ የአጠያዬቅ ዘዬም ለፕሮፌሰር ሚንጋ ሜጋ አቅም ደረጃውን የጠበቀ ሆኖ አግኝቼዋለሁኝ። በዚህ ዓመት በመቆጠብካዳመጥኳቸው ቃለ ምልልሶች ቀንዲሉ ሆኖልኛል ለእኔ። የኢትዮጵያን ክብረት እና አዱኛም ፏ ብሎ ያዬሁበት አጋጣሚ ነበር ማለት እችላለሁኝ። መስጦኛል። ተደምሜበታለሁኝ። ውስጤንም አግኝቸበታለሁኝ። ፕሮፖጋንዲስት ለማያስፈልገን ኢትዮጵያዊ ዜጎች ልካችን አግኝተናል ብዬ አስባለሁኝ። ለዚህም ነው እኔ ኢትዮጵያን በተፈጥሯዋ ልክ ያነበቡ፤ የተረጎሙ እና ያመሳጠሩ ከሳይለንት ማጆሪቲ ውስጥ ያሉ በቲም ፈላስፊቷን አገሬን ይመሩ ዘንድ ዕድሉን እንዲያገኙ እምመኜውም። ፌስ ቡኬ ላይ ለሁለተኛ ጊዜ ነው ሼር የማደርገው። ባሉኝ ሁሉ ሚዲያወቼም ብሎጌን ጨምሮ ሼር አድርጌዋለሁኝ። ከማህበራዊ ሚዲያ ርቀው ለሚኖሩ ወገኖቼም ሼር አድርጌዋለሁኝ። የጠራ አቅጣጫ ያለው ብቻ ሳይሆን አብዝቶ ቅንነትን ማዕረጉ ያደረገ መሰጠትን ስለአገኜሁበት። የጨመተ እና የሰከነ፤ እላፊ ያልሄደ ጠፈፍ ያለ የእኛነት የኔታነትን አይቸበታለሁኝ። መስታውትም ራዲዮሎጂም ማለት እችላለሁኝ። በፍፁም ሁኔታ የገረመኝ ደግሞ በኢትዮጵያ የፖለቲካ ህይወቴ ከልጅነት እስ...