#ቀናሁኝ! ኢትዮጵያ ትሰብበት! 2) እማ ሆይ! የአንችስ ቀንሽ መቼ ይሆን? የህሊና ስልጣኔ ያላስቀና ምን ያስቀናል?
#ቀናሁኝ ! የህሊና ስልጣኔ ያላስቀና ምን ያስቀናል? የሃሳብ ፋክክር #በመደማመጥ ተከውኖ #ስኬቱን ከማዬት በላይ ምን ያስቀናል? "የቤትህ ቅናት በላኝ።" ከማግኔቱ የአሜሪካ 2024 የምርጫ ፋክክር እና ክወና አቮላዊ ሙቀት ሳንወጣ ሌላም መልካም ሂደት ለማዬት በቃን። እንዲህም ሆነ …… ከጉንፋኔ ጋር እዬታገልኩኝ #የሱማሌላንድን አጓጊ እና ሳቢ የምርጫ ፋክክር በተለያዩ ሚዲያወች ስከታተል ሰነበትኩኝ። ግን ማህበረ - ቅንነት እንዴት ሰነበታችሁልኝ??? 60 ዓመት የባከነውን ጊዜ፤ ጉልበት፤ መንፈስ አሰብኩት። በፋይዳ የለሽ ብክነትም እያንዳንዳችን በግል ሁላችንም በጋራ #ብትለታችን ለዚህ መሰል ህዝበ ጠቀም አቅም አለመብቃቱ #አሳፈረኝ ። ያቺ ትንሽ በቅኝ ግዛት የማቀቀች፤ እንደኛው ድሃ በሚባሉት ተርታ የምትገኝ የአህጉራችን ቤተኛ ሱማሌላንድ ለዚህ ክብር፤ ለዚህ ልዕልና፤ ለዚህ ልቅና መብቃቷ እጅግ ደነቀኝ። እጅግም አስቀናኝ። #ቅን የፖለቲካ #ሊቃውንት እና #ሊሂቃን ያላት መሆኗንም በጥልቀት አስተዋልኩ። ከዚህ ጋር ለሰባዕዊነት ያላቸውን አትኩሮትም ተማርኩበት። ለሰው ልጅ ሰውነቱን ከማክበር፤ ለዛም ከመጠንቀቅ በላይ ምን የመሪነት ዊዝደም አለና። እንሆ ስልጡኖቹ የሱማሌላንድ ልጆች ተሳፋቸውን ሰንቀው፤ ተስፋቸውንም አሰልጥነው ጉዟቸውን በአብነት አስከበሩት። #ብርቱካኖች አሸነፋ። ብርቱካኖች ሲያሸንፋ በሰፋ ልዩነትም ነው። ገዢው ተሸናፊው ፓርቲም ሽንፈቱን ገና ሳያውቅ እኩል የፋክክር ሜዳ ፈቀደ። ይህ ልዕልና ስልጣኔ #የውሃ ልክም ነው። ሚዲያወች እኩል አገለገሉ። በመከባበር ላይ የታደመው ተፎካካሪ ህዝብ ግራ ቀኙን በጥሞና አዳመጠ። ቀኑ በጉጉት ተጠበቀ። ታዛቢወችም የደከሙበት ሂ...