ልጥፎች

ከኖቬምበር 5, 2026 ልጥፎች በማሳየት ላይ

#አለልን እንደምን እንበል?

  #አለልን እንደምን እንበል? ግን ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ የት ይሆን ያለው?   "ጥበብ ከቀይ ዕንቁ ትበልጣለችና የከበረ ነገር ሁሉ አይተካከላትም።"   #ምዕራፍ ፳።   እንደምን አደርን ሁላችንም? በዓታችንም?   #እፍታ ለአንድ አፍታ።   « #የሽብርተኝነትን ድርጊት ለመፈፀም ማቀድ፤ መዘጋጀትና ማነሳሳት።»   1) ይህ የምታዩት የክስ ምክንያት አቶ ዮናታል ተስፋዬ ረገሳ በዘመነ ህውሃት የታሠረበት የክስ ጭብጥ ነው። ወጣቱ የድል አጥቢያ አርበኛ አይደለም። ታግሏል፤ አታግሏልም።    2) ለነፃነት ተጋድሎ ከደረሰበት ዕድሜው ጀምሮ ትጋት ያለው ተግባር የፈፀመ ወጣት ነው። አልፎ አልፎ ያልተገባ ሃሳብ ስለምመለከት ነው፤ ተከሳሽም፤ ታሳሪም እንደ ነበር ለማጠየቅ ነው የተከሰሰበትን ጭብጥ ማስቀደም የፈለግሁት።   3) ሌላው ፎቶወቹ ናቸው። ፎቶወቹ ትናንት በምን ዓይነት ብሄራዊ ፍልስፍና ውስጥ መንፈሱ የተሰናዳ እንደ ነበር ይገልፃል። በሌላ በኩል ቁልፍ ቦታ በነበረው የሰማያዊ ፓርቲም ከወጣት እህት እና ወንድሞቹ ጋር አብሮ የደከመ፤ የተንገላታ፤ የበኩልን ድርሻ የተወጣ ብቻ ሳይሆን የመራም ስለመሆኑ ያመላክታል። ዝም ብሎ ከመሬት የተነሳ እና አጋጣሚ ሰጥቶት ሹመት ያገኜ አለመሆኑን በማስተዋል መመርመር ይገባል።   ወጣቶች የዘመናቸውን ታሪክ የማወቅ፤ በሂደቱም ውስጥ የነበራቸውን ድርሻ ተገኝቶም ይሁን አልተገኝቶም ዕድሜያቸውን ያበረከቱበት የተሳትፎ ሁነትን በአጽህኖት ሊዘግቡት፤ ሊማሩበት ይገባል ባይ ነኝ። በየዘመኑ በወጣቶች የመኖር #ማገዶነት ፤ የዕድሜ ግብር ውስጥ የኢትዮጵያ ፖለቲካ ማዳበሪያ መሆኑን በጥልቀት ሊገነዘቡት ይገባል። ለዕፍታ ይህን ካልኩ ቀጣዩን ንዑስ ዕርስ ላ...