ልጥፎች

ከጁን 2, 2026 ልጥፎች በማሳየት ላይ

ለእናት #ቋሚ የዕንባ ቋት መሆን ከምን ይመደብ ይሆን? ግን እቴጌ ጎንደር ስለምን #የበቀል መሞከሪያ ጣብያ ሆነች?

  ለእናት #ቋሚ የዕንባ ቋት መሆን ከምን ይመደብ ይሆን? ግን እቴጌ ጎንደር ስለምን #የበቀል መሞከሪያ ጣብያ ሆነች?   እግዚአብሄር በሚያውቀው ሚስጢር በዘመነ ኢህአዲግ የነበሩ አንቱ ሊቃናቶቿ አልቀዋል። በፋኖም በብዛት መሪወቿ አልቀዋል። "አቤቱ ንጹህ ልብ ፍጠርልኝ።" አሜን።   #ምዕራፍ ፲፱።   እንዴት ሰነበታችሁ ክብረቶቼ?    ይህን የመከራ ዜና የሚሰማ መምህር፤ ቤተሰብ እናት፤ አሳዳጊ በተለይ ሰርክ ዕንባ የታወጀለት #የህክምና #ፋክልቲ እንደምን ያስተናግደው ይሆን? ሰርክ ከእነኝህ ንጹህ ሆነው ከተፈጠሩ የህክምና ባለሙያወች፤ እጩወች ላይ ስለምን የበቀል ዱላ ተበራከተ? ከውስጤ ፈጽሞ ሊወጣ ያልቻለ የህክምና ሊቅ አለ። ሁልጊዜ የዶር አንዷዓለም ዳኜ ፎቷቸውን አየዋለሁኝ። ከህሊናዬ ሊወጡ አልቻሉም። ታትመዋል።    #ግን ጎንደር ከተማ ማን ይሆነው መሪዋ?   በኢትዮጵያ መማር፤ ጥበብን መፍቀድ፤ ስፖርትን መውደድ፤ ሙዚቀኛ - ተዋናይ - ጋዜጠኛ ጸሐፊ መሆን፤ ወይንም ፖለቲከኛ መሆን፤ ሃኪም መሆን፤ #ሰው ሁኖ መፈጠር እራሱ መከራ ነው? እንደምን ይህ #ሰንሰለታማ #የቂም እና #የበቀል ሂደት ሊቆም እንደሚችል አላውቅም።   በጣም ብዙ፤ እጅግ ብዙ በህክምና ዙሪያ የሚተጉ ተደግመው የማይገኙ የህክምና ስፔሻሊስቶች ልክ እንደ ዶር አንዱዓለም ዳኜ ዓይነት #በስጋ ተለይተዋል። በሰው እጅ #ሰማዕትነትን ተቀብለዋል። በርካታ ትዳር ፈርሷል። በርካታ ልጆች ያለአባት ወይንም ያለ እናት ቀርተዋል። ለዚህ ጉዳይ ብቻ ጸሎት፤ ሱባዬ ያስፈልጋል ብዬ የፃፍኩትም ከዚህ ቀደም ለዚህ ነበር።    #ይህ አንድ ሃዘን ብቻ አይደለም።   ጎንደር እንደ ልማዷ #...

#ጊዜን ያላባከነ ሰብዕና #ሞተ አይባልም። ትውልዳዊ #አሻራው ይቀጥላል እና።

  #ጊዜን ያላባከነ ሰብዕና #ሞተ አይባልም። ትውልዳዊ #አሻራው ይቀጥላል እና።   ለመላ ቤተሰብ መፅናናትን እመኛለሁኝ። ለክቡርነታቸው ነፍሳቸውን በአጸደ ገነት ያኑርልን። አሜን። ሚዲያው ለሰጠን መረጃም አመሰግናለሁኝ።    ሥርጉትሻ 28/05/026።   ከሸገር ኤፍኤም ነው መረጃውን ያገኜሁት።    "ግንቦት 19/2018" "በደርግ ዘመነ መንግሥት የተሰሩ ትላልቅ ፕሮጀክቶችን በመምራት የሚታወቁት አቶ ካሳ ገብሬ ከዚህ አለም በሞት ተለዩ። አቶ ካሳ በ92 ዓመት እድሜያቸው ይኖሩበት በነበረው አሜሪካ ሀገር ህይወታቸው ያለፈው በዛሬው እለት ነው።   ኢንጂነር ካሳ ገብሬ ከኢትዮጵያ ህንፃ ኮሌጅ በሲቪል ምህንድስና ካናዳ ሀገር በሚገኘው የብሪቲሽ ኮሎምቢያ ዩኒቨርሲቲ የአንድ ዓመት የድህረ ምረቃ ትምህርታቸውን መከታተላቸውን የህይወት ታሪካቸው ያስረዳል።    በትምህርት ሚኒስቴር በዋና መሃንዲስነት፣ በቤቶችና ከተማ ልማት ሚኒስቴር ሚኒስትርነት፣ በኤርትራ የጠቅላይ ግዛቱ ዋና መሃንዲስ፣ በሕንጻ ኮንስትራክሽን ሚኒስትርነት እና በተለያዩ ከፍተኛ የመንግሥት ኃላፊነቶች እስከ ደርግ ስርዓት ማብቃት ድርስ አገልግለዋል። ኢንጂነር ካሳ በደርግ ስርዓት ወቅት የተሰሩ ትላልቅ ፕሮጀክቶችንም መርተዋል።    በሶማሌ ወረራ ጦርነት ወቅት ህዝባዊ ሠራዊት የሰለጠንበትን የታጠቅ ጦር ሜዳ ግንባታ በአጭር ጊዜ ውስጥ ማዘጋጀታቸው ከሚጠቀስላቸው ስራዎቻቸው መከከል ይገኝበታል።    የጀግኖችና ህፃናት አምባ ምስረታዎች ወቅት የግንባታ ዘርፉን መርተዋል።    የጣና በለስ ግድብ፣ የቀይ መስቀል ሕንጻ፣ ዋቢ ሸበሌ ሆቴል፣ ፍልውሃ ሕንጻዎች፣ አክሱም ጽዮን ቤተክርስቲያን፣...

#ኢትዮጵያ እንዲህም ናት። #መምህር ናትና።

  #ኢትዮጵያ እንዲህም ናት። #መምህር ናትና።    https://www.youtube.com/watch?v=Xm14vSdXkLc&t=216s     ስለአባቷ አዲስ ነገር ተናገረች ፥የፀገነት ታሪክ ቀጥሏል #story #ethiopianpodacst #lovestory   እሙኃይ አለምነሽ እና ልጃቸው ወጣት ዕፀገነት ብርሃኔ። #ፈጣሪ በፈጠረው የእናት እና የልጅ ፍቅር፣ #ፈጣሪ በፈጠረው ፍጹም ታማኝነት ልክ። #ፈጣሪ በፈጠረው መከራን ታግሶ የማሳለፍ ልክ። #ፈጣሪ በፈጠረው ልክ የጊዜ ቁምነገር የተረጎመበት መክሊት። #ፈጣሪ በፈጠረው ልክ የጋብቻን በኽረ ተፈጥሯዊ ህግ በመፈጸም ………   "አቤቱ የቤትህ ቅናት በላኝ። "   ክፍል ሁለት ላይ ዕፂ ዘማሪ ለመሆን ወስናለች። በሌላ በኩል "እንኳንም ኢትዮጵያ ተወለድኩኝ። እንኳንም ኢትዮጵያዊ ሆንኩኝ።" የሚል ኃይለ ቃል ተናግራለች።    ኢትዮጵያ እንዲህ ናት። ወንጌሉ እንደሚለው በአንድም፣ በሌላም ታስተምራለች። #ወደ 5ሺህ የሚሆን ስልክ ተደውሎላት ከኢትዮጵውያን እና ከኤርትራውያን፣ ችላ ያነሳችው #ሥማቸውንም የመዘገበችው ከ1500 በላይ ነው።    ስለወላጅ አባቷ ሥም ሆነ ክስ በብዙ አድማጭ ብትጠየቅም፣ "ቤተሰቡን አልረብሽም። እህት እና ወንድሞቼን አልረብሽም። እነሱ እንደ ሌላው ሰው ሊያደምጡት፣ አብረውን #ሊያለቅሱ ይችሉ ይሆናል። እኔም #አባቴ ሥም አልጠራም። በፍርድ ቤት አሳውቄ አስወስኛለሁኝ። በእናቴ አባት ሥም ነው የምጠራው። " በጣም የደነቀኝ የመወሰን አቅም።    "እና ሳላውቀው ይቅርታ ላደርግለት አልችልም። መጥቶ ይቅርታ ከጠየቀኝ፣ ይቅርታ አደርግለታለሁኝ። አባትነቱ ግን የለም። ልጅነቱም #የ...