ልጥፎች

ከማርች 15, 2019 ልጥፎች በማሳየት ላይ

የኢትዮጵያ በሽታ (ከጸሐፊ አቶ መስፍን ማሞ ተሰማ)

 እንኳን ደህና መጡልኝ።  የኢትዮጵያ በሽታ መስፍን ማሞ ተሰማ ሠላም ለናንተ ይሁን! እንግዲህ ምን ይሻላል? ኢትዮጵያ ውስጥ ሁሉም አጥሩን /ክልሉን እያጠበቀ አትድረሱብኝ ማለቱ ብቻ ሳይሆን እዛው ተወልደውና ከብደው ቤተሰብና ንብረት አፍርተው ለዘመናት የኖሩትንም ከደርቡሽ ወይም ከጣልያን የመጡ ይመስል - ወራሪ፤ መጤ፤ ሰፋሪ - እየተባሉ ማቄን ጨርቄን ሳይሉ በአንድ ጀንበር ከነ እንቦቃቅላ ህፃናት ጭምር <የመሬት ባለቤት ነን> ባዮች (ክልላዊ መንግሥታትና ራስ ገዝ ቡድኖች) በግፍ ሲያባርሩና ሲገድሉ <ለተፈናቃይ ሀገር በቀል ስደተኞች> በወቅቱና በተገቢው ሁኔታ የሚደርስላቸውም ሆነ በተግባር የሚቆረቆርላቸው <መንግሥት> አለመኖር ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተባባሰ መሄዱ እጅግ አስጨናቂ ክስተት ሆኗል። <ባለ መሬት ነን> ባዮቹንም ሃይ የሚል የመንግሥት ሃላፊ የለም። እንደውም በግፍና ያለ ህግ የተፈናቀሉትን <ለኛ ፖለቲካ በሚጠቅም መልኩ አስፍረናቸዋል> ያሉ <እንደ ሃይማኖት እናምናቸው የጀመርናቸው የለውጡ <ፊታውራሪዎች ኢትዮጵያዊ መሪዎች> ሲናገሩ ከመስማትና ከማየት በላይ ለሰማይም ለመሬትም የከበደ በደልና ሀጢያት ከቶ ከወዴት ሀገር አለ? ይህ ሁሉ ሰቆቃ የሚፈፀመው ደግሞ የ<ህገ መንግሥት> ሰነድ አይናችን ላይ እያወዛወዙና <ኢትዮጵያዊነት ሱስ ነው> እያሉን መሆኑ ነው። እንግዲህ <ህገ መንግሥቱ> ለዘረኝነትና ለአፓርታይዳውያን መሳሪያነት የቆመ ጠበቃ ነው ብንል ሀሰት ይሆናልን?!    <ብሄር ብሄረሰቦችና ህዝቦች> የሚለው ቅጥ አምባሩ የጠፋና ትርጉሙም ፍንትው ብሎ በማይታወቅ <አብዮታዊ ዲሞክራሲ> ንድፈ ሀሳብ አጥ...