ልጥፎች

ከፌብሩዋሪ 25, 2026 ልጥፎች በማሳየት ላይ

#ስሜናዊነቴ ህወሃትን ቤቴ ለማለት ከሆነ በአፍንጫዬ ይውጣ።

  #ስሜናዊነቴ ህወሃትን ቤቴ ለማለት ከሆነ በአፍንጫዬ ይውጣ።   "አቤቱ ንጹህ ልብ ፍጠርልኝ።" አሜን።   #ምዕራፍ ፲፰።   #እፍታ ለአፍታ። አወን እርግጥ ነው በአባቴም በእናቴም ስሜናዊ ነኝ። ስሜናዊነቴ አንዱ ማንነቴ ነው። ግን ያን ጊዜ የማይስተምረውን የጭካኔ አስኳል ጋር ለሠርግ - መልስ፤ ለቅልቅል እና ለግጥግጥ ከሆነ ስሜናዊነቴ በአፍንጫዬ ይውጣ።   የሚገርመኝ የጽጥምዶ ባላንበራሶች ዛሬ ደርሰው የወልቃይት፤ የጠገዴ፤ የአዲረመጥ፤ የአዳርቃይ፤ የጠለምት፤ የራያ ተቆርቋሪ ሆነው መምጣታቸው ነው። እንደ ሽንብራ ቂጣ መገላበጡ የእውነትን ልክ #ሊከልሰው ፈጽሞ አይችልም።   ዛሬም ህወሃት ከዛ #ከታቆረ ሃሳቡ ፈቀቅ ሊል ያልቻለ፤ ድውይ ድርጅት መሆኑ ዓለምም እያዬው ነው። ኡኡታው፤ ለማሳጣት ከፍ ዝቅ ማለቱ፤ መሸነፋን ለመቀበል አቅል አጥቶ መክለፍለፋ ዘመን ሊያስተምረው አልቻለም። እንጂማ ቢገባው የእሱ አንቱነት ከግንቦት መግቢያ 2023 ጀምሮ ማክተሙን አላወቀም።    #ለማንኛውም ሰብ ይሁን ተቋም እኔ የምለው ……   1) መውደቅን መቀበል ብልህነት ነው። መሸነፍን መቀበል ብልህነት ነው። ምክንያቱም በመውደቅ ውስጥ መነሳት፤ በመሸነፍ #ከርስ ውስጥ ማሸነፍም ስለሚቻል።   መሸነፍ ብቻውን አይቆምም። የሙሉ ዕድሜ ተመክሮ መግቦ ነው። በመሸነፍ ውስጥ እራስን የማየት አጋጣሚ ይገኛል። መሸነፍን ለሚቀበል። ዕውቅናም ለሚሰጥ። ይህ ሲሆን በመሸነፍ ውስጥ ዳግም ጥፋትን ላለማጨት ህሊናን ያሰናዳል።   2) መውደቅም ቢሆን ከብዙ ኪሳራ ጋር ቢሆንም፤ እራስን ከወደቁበት ረግረግ ለማውጣት የጥሞና፤ የተደሞ ጊዜ ቢሰጠው በአዲስ አቅም፤ በእሸት ጉልበት አገግሞ ቀና ማለት ይቻላል። ግን ...

ቅጽበታዊው #ስምረት ፓርቲ ገና ጮርቃ እኮ ነው። በደል ይረሳል ወይንስ #ይለመዳል? አዲስ ልብስ #የጭካኔን ገመና አይሸፍንም።

  ቅጽበታዊው #ስምረት ፓርቲ ገና ጮርቃ እኮ ነው። በደል ይረሳል ወይንስ #ይለመዳል ? አዲስ ልብስ #የጭካኔን ገመና አይሸፍንም።   "አቤቱ ንጹህ ልብ ፍጠርልኝ።" አሜን።   #ምዕራፍ ፲፰።   #ጠብታ ።   እኔ ሥርጉተ ሥላሴ የአዳዲስ የፖለቲካ ድርጅት ምሥረታ የሚያስፈነድቀኝ፤ የአዳዲስ የፖለቲካ ድርጅቶች ምርጫ በመጣ ቁጥር በአዲስ ማራኪ ሥያሜ መዋህድ ይሁን መቀናጀት ፋሲካዬ ነው ብዬ አቅም የማባክን ሰው አይደለሁም። ይህን አፍንጫህን ላስ አቶ ሂደት ላይ ጽፌዋለሁኝ ሌላ ጊዜም ስለ አጤ ሂደት እንዲሁ ጽፌለሁኝ። በከንቱ እምናፈሰው አቅም ቁስ ጉዳይ አይደለም። እሱ ቀላል ነው። መኖሩን በእስር፤ በመታገት፤ በመሰወር፤ ነፍሱን በማጣት ለሚቀማው ትውልድ ጠቃሚ መንገድ አለመሆኑን ቀድሜ ተረድቸዋለሁኝ። ትርፈ ቢስ አልቦሽነቱን ትርጉሙም፤ ሚስጢሩም ገብቶኛል። እንኳን መላ አካለት በጭካኔ፤ በመታበይ በዝና ሱስ፤ በሚዲያ ንግሥና መውደቅ መነሳት ላይ አቅም ላባክን።   #ቆባ ላይ ያለ ድርጅት ልኩን በልኩ ቢያደርገው።   የአባ ሻንቆ ፍታውራሪ አርበኛ መለሰን በዓት ትናት የተፈጠረ ሩብ ዓመት ያላስቆጠረ የፖለቲካ ድርጅት ለዚህ ግዙፍ ሚስጢርን አቅፎ ለተቆረቆረ በዓት ባለቤት ነኝ ብሎ ሲነሳ ከትከት ብዬ #ስቄያለሁኝ ። ያን ሁሉ የማይካድራ ደም በከንቱ ያፈሰሰ፤ በድፍን ወሎ፤ በወገራ ጭና፥ በንፋስ መውጫ የፈጸመው ሞልቶ የተረፈው ግፍ ሱፍ አስለብሶ በሽልማት፤ በሽርሽሽር፤ በሰርግ መልስ እና ቅልቅል ድለቃ ትወና ዓይን አይችለው የለ ሚዲያ ግልምት እስኪለን ድረስ አየን። ማፈሪያነት፤ ጸረ ሰውነት ባለ ክብር ሆኖ ሲጎማሸር የኢትዮጵያ ፖለቲካ ለሰብአዊነት፤ ለተፈጥሯዊነት ያለው የህሊና አቅምን ፍንትው አድርጎ ያሳያል። ...