ልጥፎች

ከሜይ 30, 2024 ልጥፎች በማሳየት ላይ

አንድ አገር ጥበብነን ካሰረ ዓይኑን ግርዶሽ ይዞታል ማለት ነው

ምስል
      አንድ አገር ጥበብነን ካሰረ ዓይኑን ግርዶሽ ይዞታል ማለት ነው። ጥበብ እኮ የተሰወረን ክሱት የምታደርግ። ጠማማን አቆላምጣ የምታስተካክል። ዘባጣን አባብላ የምታርቅ የህሊና ጋራጅ ናት ላወቀበት። ግን ተፈራች። እስቲ ግርማ ሌሊቱን አምላካችን ይባርክልን። አሜን ደህና እደሩልኝ። ሁሉንም አስተያዬት አይቼዋለሁኝ። እግዚአብሄር ይስጥልኝ። ሥርጉ2024/05/29

ትጉህ

ምስል
 

እንዴት አደራችሁ? ዕለታት ሁሉ ውብ ናቸው።

  እንዴት አደራችሁ? ዕለታት ሁሉ ውብ ናቸው። የምናከፋቸው እኛው ነን። ከሁሉ የሚደንቀኝ ግን ቅን ሰው ያገኜሁበት ዕለት ነው። ቅኖች ያላቸውን ሁሉ ያለገደብ ይሰጣሉ። ቅኖች ልግሥናቸው ከፀጋ ስጦታቸው ነውና ዳር ድንበር የለው። ሥርጉትሻ 2024/05/30

ከእራስ ጋር እርቀ ሰላም ሳይደረግ ቤተሰብ ይመሰረታል።

  ከእራስ ጋር እርቀ ሰላም ሳይደረግ ቤተሰብ ይመሰረታል። ባለፈም ህዝብ መሪነትም ይወሰዳል። መጀመሪያ እኔ እና እኔ በጥሞና ቁጭ ብለን ተነጋግረን እንፈራረም። ሥርጉትሻ2024/05/30

ጥሞና እባክህ ና!

 ጥሞና እባክህ ና! ሥርጉትሻ2024/05/30

ቀን የበደለው የለም

  ቀን የበደለው የለም። ቀኑን በዳይ አስፈሪ የሚያደርገው ፖለቲካው ነው። ስለሆነም ፖለቲካው ከአስፈሪነቱ ጭካኔ ጋር መፋታት ይኖርበታል። ስጋት የናጠው ህዝብ የሥነ - ልቦና ተጠቂ ይሆናል። ሥርጉ2024/05/30   ቀን የበደለው የለም። ቀኑን በዳይ አስፈሪ የሚያደርገው ፖለቲካው ነው። ስለሆነም ፖለቲካው ከአስፈሪነቱ ጭካኔ ጋር መፋታት ይኖርበታል። ስጋት የናጠው ህዝብ የሥነ - ልቦና ተጠቂ ይሆናል። ሥርጉ2024/05/30