ልጥፎች

ከጁላይ 25, 2022 ልጥፎች በማሳየት ላይ

"ሞት አያምም።" (ከእሸት ባለቅኔ ከገጣሚ በላይ በቀለ ዋያ።) 25.07.2022

ምስል
የቁም እስረኛው ገጣሚ የጨመተ ፀጋው ህሊናዬ። የማህበራዊ ሚዲያው ንቅናቄ ቴርሞሜትር። መንግሥት የሸፈተባት አገር። "ሞት አያምም" እኖር ብዬ ብታረድም ለመኖር ስል ብሰደድም እኖር ብዬ ብዋረድም ዘጠኝ ሞቴን ብሞታት አንዴ እንደ መኖር አይከብድም። መኖር ከሞመት አይልቅም ሞት እንደ ሕይወት አይጨንቅም። "ምክንያት" "የሞተ እሞታለሁ ሲል አያውቅም በጭራሽ ፈርቶ ያልኖረም አያውቅም ሞቶ መኖሬ እንጅ የሚያስፈራኝ መኖር እንጂ *የሚያስገባኝ መኖር እንጂየሚያስከፋኝ መኖር እንጂ የሚበድል ሞት አያምም *ከቆሰለ ሞት አያምም ከገደለ።" * ድምፁ ስለሚዋጥ ያልተሰሙኝ ናቸው። ግድፈት ካለበት ገጣሚ ባለቅኔም በላይ በቀለ ወያን ይቅርታ እጠይቃለሁኝ። የገጣሚ በላይ በቀለ ዋያ ድንቅ ቅኔ ነው ሥንኙ። መኖርን የሞገተበት። ሞነርን ችሎት ላይ እንዲህ ገትሮልኛል። ተባረክ የእኔ ጌታ። 'የቤትህ ቅናት በላኝ።" የውስጤን ስገልፀው - እኔው። ብዕር ታሰረ በጭካኔ ተወረረ ተመረመረ እንደ አልባሌ ተባራረ እዬተከረከረ እያከራከረ ቆሽቱ እያረረ የብራና ጠብታ የዘመን ምጣት ቱማታ በመታበይ ተመታ። #የቃለ ምልልሱ ጭብጥ ከውስጤ ሳወያዬው መሰጠኝ፣ ጣመኝ ቃናውም ቁመናውም - እኔኑ። "በሥራም በትንቢትም አምናለሁ ተስፋ አደርጋለሁኝ። ሰው ለምን አስከፋኝ ብዬ አላውቅም። እኔ ምን አሰከፋሁት እንጂ።" "ህገወጥ ህጋዊነቱ ያስፈራኛል" "የግነት ሁነት በውስጤ እንዲኖር አልፈቅድም። በታፈንኩበት ክፍል የነበሩ ሰወች መልካሞች ነበሩ።" "ወላጆቼ ባይኖሩ ነፃነቴን ስለምወድ አስቸጋሪ እሆን ነበር።" "ስለ እኔ በጎ ምልከታ የሌላቸውን አላስባቸውም። መልካሞች ስለሚበዙ።" &