ልጥፎች

ከኖቬምበር 23, 2024 ልጥፎች በማሳየት ላይ

ድርድር የሰላም መቅኖ ነው። #የበኽሩ ድርድር የእውቀት ዘርፍ ነው። ብልሆች በፀሎት // በድዋ ከከወኑት እዮራዊ በረከትም ነው። ለተጨነቁም ፈጥኖ ደራሽ።

  #የበኽሩ ድርድር የእውቀት ዘርፍ ነው። ብልሆች በፀሎት // በድዋ ከከወኑት እዮራዊ በረከትም ነው። ለተጨነቁም ፈጥኖ ደራሽ።   "የሰው ልብ መንገድን ያዘጋጃል፤ እግዚአብሄር ግን አካሄዱን ያቃናለታል።" (ምሳሌ ፲፮ ቁጥር ፱)   ከማገዶወች ውስጥ የተወሰኑትን አቅር ቤያለሁኝ። ስማቸው እና ተግባራቸው አደባባይ ስለወጣ እንጂ ከ10 - 20 ሺ የሚጠጉ የአማራ ልጆች በአፋር በረሃ እንደታሰሩ አድምጠናል። እነኛ ምንዱባን ምን እንደ ገጠማቸው በተጨባጭ እምናውቀው ነገር የለም። የትኞቹ በህይወት ይኑሩ፦ የትኞቹ አካላቸው ጋር ይኑሩ፤ የትኞቹ በጤናቸው ላይ እክል ይግጠም እምናውቀው የለም። መሬት ላይ አማራን የሚወክል ተቋም የለም እና። በሌላ በኩል በሌሎች ክልሎችም ከፋኖ ጋር በተያያዘ የታሰሩ የአማራ ሊቃናት ሊኖሩ ይችሉ ይሆናል። በአማራ ክልልም የአማራ ልጆች ማሰቃያ #ማጎሪያ የአገር ውስጥ #ስደተኛ ካንፕ መሰራቱን ቢቢሲ የአማርኛው መረጃውን አጋርቶናል።   በሌላ በኩል በግል እስር ቤትም የሚኖሩ መከረኞች ይኖራሉ። በተለይ #ገላን እና #አዲስ አበባ። ህወሃት በገነባቸው የማሰቃያ ቀደምት እስር ቤቶችም በርካታ ትጉህ የአማራ ሊቃናት አሳራቸውን እያዩ ነው። እስረኞች ቤተሰብ አላቸው። ልጆችም ይኖራቸዋል። ትዳርም ይኖራል። ያቺ ዘመን ከዘመን በቃሽ ያላላት/// የማይላት አንድዬ የአማራ #እናትም አለችበት። መኖር + ስጋት ታክሎ የአማራ መላ ቤተሰብ በግፍ እዬታረሰ ነው። በኢኮኖሚ የተሻሉት ከተሞችን በማንደድ አብሮ በማደህዬት ፕሮጀክት ዛሬ እንኳን ለሌላ ለራስም አልሆን ብሎ የሰው እጅ ተመልካች የሆኑ ከስድስት አመት በፊት ግን የፕሮጀክት ባለቤት የነበሩ የአማራ ልጆች በርካቶች ናቸው። ጫካ የገቡትም የፋኖ ታጋዮች ቢሆኑ ቤተሰብ ይኖራቸዋል...