ልጥፎች

ከኖቬምበር 29, 2024 ልጥፎች በማሳየት ላይ

የፍቅር ተፈጥሮ ስልጣኔ ማስተዋል ነው። Die Natur der Liebe ist zivilisiertes Verständnis.

ምስል
Für mich ist die Natur der Liebe Wissenschaft. Es ist auch eine Philosophie. ለእኔ የፍቅር ተፈጥሮ ሳይንስ ነው። ፍልስፍናም ነው።

#ብክነት ካለ #ስኬት፦ ግን #በማገዶነት። የኢህአፓ እስረኞች ፎቶውን ብሎጌ ላይ አይፈቀድም። ግን ፌስቡኬ ላይ አለ።

  #ብክነት ካለ #ስኬት ፦ ግን #በማገዶነት ።  https://www.facebook.com/sergute.selassie/   "የቤትህ ቅናት በላኝ። "   የመዋለ ዕድሜ የኢህአፓ አባላት በአገራቸው ግዞተኛ ናቸው። ማፍቀር፤ መዳር - መኳል፤ መውለድ - መሳም፤ ዘር መተካት፦ ዓይንን በአይን የማዬት ሃሴት ተፈጥሯዊ ሂደቱም እስረኛ ነው። የቤተሰብ፦ የማህበራዊ ኑሮም፥ ጤናማ ግንኙነት ድፍርስ ወይ ያጎረፈ፦ ያጎፈረም ነው። በፖለቲካ የሚሳተፍ ትጉህ ሁልጊዜም ይገለላል ጥቃትም ይፈፀምበታል። ከዚህ አስፈሪ ሂደት ነገ ትውልዱ ምን ይማርበታል???   እነኝህ ምንዱባን በዘመነ ደርግ የኢህአፓ ታጋይ አፍለኛ ወጣት የነበሩ ይመስለኛል። #ሴት እህታችንም አለችበት። በዛ ዘመን ሴቶች ደፍረው ወደ ትግል መግባታቸው በራሱ ለኢትዮጵያ የፖለቲካ ታሪክ #ጌጥ እንጅ እንደ ዕዳ ባልታዬም ነበር። ህሊና ቢኖር። አሳረኞቹ በዘመነ ህወሃት ታሠሩ፤ በዘመነ አብይዝም እስሩ ቀጠለ። ግዞተኛ በባዕት።   እኔ የታገልኩት የፖለቲካ እስረኛ #የክት እና #የዘወትር እስረኛ ዘመን የሰጠው ገዢ እንዲኖረው አልነበረም። የሚገርመው በዘመነ ህወሃት ከነበረው በናረ ሁኔታ በዘመነ አብይ የፖለቲካ እስረኛ ኢትዮጵያ ውስጥ አለ ከምል ተጥለቅልቋል ብል ይሻላል። ለዛውም በበቀል የተቁላላ፤ በቅሬታ ክምችት የተቀመመ። የሚገርመው የዚህኛው የጭካኔው ስታይሊንግ ከነበሩት ገዢወች የተለዬ፤ ያልተለመደ መሆኑ ነው።    በዚህ ዘመን የሚያስደነግጡ የአረማዊ ክንወኖች ያለፋታ ህሊናችን እንዲሸከም መገደዱ ስለ ሰብ ይመለከተኛል የሚል ሁሉ አብሮ መንፈሱም፤ ጤናውም እንዲደቅ ተደርጓል። በምንኖርበት የስደት አገርም ትናንትም ያሳድዱናል፤ ዛሬም ያሳድዱናል። ለምን? ያ...