ልጥፎች

ከኦክቶበር 14, 2018 ልጥፎች በማሳየት ላይ

አቶ ዳውድ ኢብሳ የኢትዮጵያን መንግሥት እያስደገደጉት ነውን?

ምስል
አቶ ዳውድ ኢብሳ  የኢትዮጵያን መንግሥት እያስደገደጉት ነውን? „አንተን በፍራሃት ወደ ቅድስናህ መቅደስ እሰግዳለሁ።“ መዝሙር ምዕራፍ ፭ ቁጥር ፯ ከሥርጉተ©ሥላሴ 14.10.2018 ከጭምቷ ሲዊዘርላንድ። አቶ ካሳሁን ጎፌ መግለጫን የገባኝን ያህል ስጥፈው ቆፍጠን ያለ ነው ድፍረቱ ከኖረ ብዬ ነበር። አቃለው አሳንሰው ሲዩትም ደግሞ አይደለም ለኢትዮጵያ ብቻ ሳይሆን ለመካከለኛው ምስራቅም አስጊ ነው ብዬ ነበር። የአፍ ወልምታ ለተባለውም ያልኩትን ብያለሁኝ። ሲጀመርም እኔ የአቶ ዳውድ ትምህክት መሰረት እንዳለው፤ በቀላል መታዬት እንደሌለበት ሞገደኛ እና ከባድ ውሳኔ ስለመሆኑ ገልጫለሁኝ። የ5ቱ የ ኦሮሞ ድርጅቶች ውሳኔም ከዚህ ጋር የሚዋደድ ነው። አሁን ፕ/ ኢሳያስ አፈወርቂ በስኳር ፖለቲካ ኢትዮጵያ እንደ ገቡ አዳመጥኩኝ። ፍቅሩን ያሰንብትላቸው እንጂ እፍ ብለዋል። የጣሊያኑ መሪ ወደ ዛው አቅንተው እንደ ነበርም አድምጠን ነበር። እና ተመለሱ ይሆን ወይንስ ምጥዋ ላይ ተበለስ ጋር? ከዙፋን አስወርዶ በጥድፊያ ያሰመጣው የኤርትራን መንግሥት ምን ቢኖር ነው ብለን ማሰብ ግድ አለን። ደረታቸው ነፍተው ሲናገሩ የሰነበቱት አቶ ዳውድ ኢብሳ በሦስተኛ አገር ሽምግልና ከልሆና በጅ አልልም ያሉ ይመስላል። ሌላ ከሚመጣም ወዳጃቸው አገር ብትሆንላቸው ይሻላቸዋል። ነገም በ አገርነት እንቀጥላልን ባይም ናቸው። ወጣት መሪም ታች ካለ በቂ ነው ብለዋል። ምርጫው የሳቸው ነው። ማን ደፍሮ ይናገራል ጭጭ ረጭ ሆኗል። ከእትጌ ኤርትራ ቤት ዘው ከተባለ መውጫ የለም፤ ወይ መዋጥ ወይ አብሮ መስመጥ ነው … ግን ኢትዮጵያን ማን ነው እዬመራት ያለው? በኢትዮጵያ ፖለቲካ ላይ ኤርትራ ታጣዋለች ተብሎ የታሰበው ረጅም እጅ ይሁነኝ ተብሏል።...