ድንግል ሆይ! ጋዜጠኛ አበበ ገላውን ጠብቂልን! አደራ!
እንኳን ደህና መጡልኝ ድንግል ሆይ! ጋዜጠኛ አበበ ገላውን ጠብቂልን! አደራ! „ኃጢያትን ተዋት እደ ልቦናህ አቅና፤ ልቦናህንም ከኃጢያት ሁሉ አንፃ“ ምዕራፍ ፴፰ ቁጥር ፭ ከሥርጉተ©ሥላሴ Sergute©Selassie 26.03.2019 ከእመ ዝምታ። ጤና ይስጥልኝ ውዶቼ እንዴት ናችሁ? ደህና ናችሁ ወይ? የማይሰማ ነገር የለም። ሌላ ሰው ቢናገረው ምንም አይደንቀኝም። አቶ ኤርምያስ ለገሰ በጸሐፊነትም፤ በም/ሚር ማዕረግም፤ በድርጅት አባልነትም የበቃ ተመክሮ ያለው ሰው ነው። መምህርም ነው። መምህር ሰብዕናው ለሁሉም አባትነት ይመስለኛል። አቨይ አባቴ እንደዛ ነበር። ነገር ግን ይህ ነገር ያዳመጥኩት አመክንዮ እሱን የሚገልጥ አልመስል አለኝ። ጋዜጠኛ አበበ ገላውን አሳልፎ የሚያሰጥ መረጃ ሜዳ ላይ ዘክዝኮታል። ዘርግፎታል። ሞትም ፈርዶበታል ያ ጥቃት ያወጣ ጋዜጠና። እጅግ ያስደነግጣል። እንዴት ጓዱን አሳልፎ ይስጣል። ለዛውም በዚህ ቋያ ጊዜ። የኃይል አሰላለፉ ባልጠራበት ወቅት። ጓድን፤ ክፉ ደጉን አብሮ አሳልፎ፤ ጥቃትን ላወጣ ወንድም እንዴት በአደባባይ ሞት እንዲፈረድበት ይደረጋል። እያንዳንዱ ሰው እኮ ለራሱ ሰብዕና ጠንቃቃ ነው። ለዛውም ጠ/ሚር አብይ አህመድ አሁን እደማያቸው ከሆነ አይደለም ሰብዕናቸውን የሚንድ ትችትን እንኳን ለማስተናገድ የሚፈቅዱ አልሆነም። ጫን ያለ መከራ ከፊታችን ተደቅኗል። እንኳንስ ይህ በጠቅላላ በሥልጣናቸው የመጣ ጉዳይ ... https://www.youtube.com/watch?v=0nWgC-QijJg ESAT Eletawi Part Two Mon 25 Mar 2019 1 ለመሆኑ ትውልድ የማይተካው ያ ትንታግ የጀግኖች ቁንጮ አንበሳ፤ የወን...