ልጥፎች
ከዲሴምበር 12, 2020 ልጥፎች በማሳየት ላይ
- አገናኝ አግኝ
- ፌስቡክ
- X
- ኢሜይል
- ሌሎች መተግበሪያዎች
እንኳን ወደ ቀንበጥ ብሎግ በሰላም መጡልኝ። „የሰው ልብ መንገድን ያዘጋጃል፤ እግዚአብሔር ግን አካሄዱን ያቃናለታል። ምሳሌ ምዕራፍ 16 ቁጥር 9“ # የቅዱስ የሖንስ የተስፋ አቤቱታ ለጠቅላይ ሚኒስተር አብይ አህመድ፡ አዲስ አበባ። # እፍታ። ጤና ይስጥልኝ ዶር አብይ አህመድ እንዴት ሰነበቱ? ተለያይተን ባጀን። እርስዎ ስለፈቀዱት። የፓርላማውን ዘገባዎትን ከውስጤ አዳምጬ በ9 ምዕራፍ ሞገትኩዎት ከሁለት ዓመት በኋላ። በማግስቱ አንድ ቀን ፌስቡክ አግዶኝም ዋለ። እባክዎት ማስረን ሆነ ማሳሰርን አይፍቀዱት። አይበጅም እና። የሆነ ሆኖ ከውስጣቸው ካዘኑበዎት ሰዎች አንዷ እኔ ነኝ እና ከውስጤ አዳጬዎት አላውቅም ነበር። በውነቱ ያን ቀን የተሻለ መንፈስ ነበረኝ። ያስታውሱ እንደ ሆን በግንቦት መግቢያ 2010 ዓ.ም እኔም ኢትዮጵያዊ ከሆንኩኝ ብዬ „አብይ ሆይ!“ የሚል ዘለግ ያለ አቤቱታ አቅርቤለዎት ነበር። ትንሽ ትንሽ ስለሚያዳምጡም የተወሰነ ነገር መከወነዎትን አይቻለሁኝ። የአቶ ኦባንግ ሜቶ ሆነ በሌሉበት እስከ ሞት ፍርድ የተወሰነባቸው ወገኖቼ ክስ መሰረዝ ምን ያህል እንደ ጠቀመዎት እርስዎ ያውቁታል። ብዙ ነገር ሸፍኖሎወታል። ጋርድሎዎታልም። እስቲ ከቻሉ አይደክመዎትም እና አብይ ሆይን ደግመው ቢያነቡትም ብዙ ነገር ያገኙበታል - ይጠቅመዎታልም። ስለ ወሮ/ፈትለወርቅ፤ ስለ ባህላዊ የጎንደር የትጥቅ ትውፊት የአገር ዘብነት፤ ስለ አማራ ታማኝነት ወዘተ … ብዙ ቁም - ነገሮች የከተቡኩበት ጹሑፍ ነበር። የሆነ ሆኖ ያን ጊዜ ከምርጫ በፊት ምንም አቤቱታ ላለቀርብ ቃል ገብቼለዎት ነበር። እንዲህ በርቀት እንለያያለን ብዬ አላሰብ...