ክፍል ሁለት ማጠቃለያ፤ ዓይነ ጠባብነት!
ወጣቶች እንደ 66ቱ ዘመን ዓይነ ጠባቦች መሆን አይገባቸውም። ክፍል ሁለት ማጠቃለያ። ከሥርጉተ ሥላሴ 29.06.2018 (ከገዳማዊቷ ሲዊዘርላንድ) „የወይን ጠጅ ፌዘኛ ያደርጋል፤ ብርቱ መጠጥም ጠበኛ ያደርጋል፤ በዚህ የሳተ ሁሉ ጠቢብ አይደለም“ (መጽሐፈ ምሳሌ ምዕራፍ ፳ ቁጥር ፩) · እፍታ ዛሬ ነው ከብራና ሳተናው የገባሁት። ትናንትና በተከታታይ የጻፍኳቸው የሰቆቃው አማራ ጉዳይ እና የእውነት ጠበቃ ማጣት በሚመለከት ስጽፍ ስለዋልኩኝ ጊዜ አልነበረኝም። · መነሻዬ። አሁን ዛሬ ሳተናው ብራና ላይ የኢሳቱ ጋዜጣኛ አቶ መሳይ መኮነን የመደመር ፖለቲካ አስፈርቶታል። „ ከዚህ አንዳንዶች ባይደመሩስ ?“ ( መሳይ መኮነን ) June 27, 2018 https://www.satenaw.com/amharic/archives/59493 „አንዳንዶችስ ባይደመሩ ይለናል?“ ትንታጉ ጋዜጠኛ። ጽዋው የማንፌሰቶ ማህበርተኝነት ነው። ሌላ ቁምነገር የለውም። መልካም ነገር ግን ብሄርም፤ ፖለቲካም፤ ማንፌስቶም የለውም። የሆነ ሆኖ የኔዎቹ ማጠቃለያው እንሆ። የይቅርታ ልብ ሳይኖረን ለውጥ ያማል። ንጹህ ልብ ሳይኖረን ኢትዮጵያዊነት ይጎመዝዛል። ኢትዮጵያ ሰፊ አገር ናት ሁሉንም እንደ አመሉ የመቻል አቅም ችሎታ ክህሎት አላት። ሰዎች በደከሙበት የመደመር ዕልፍኝም ቤተኛ እና ተርተኛ ይለይ ይከብዳል። ሁልጊዜ በ አጥር ተከልሎ ሁልጊዜ ቂምን ተጠልሎ ሁልጊዜ ቋስን እርሾ አድርጎ ተውልድን መገንባት ጋዳ ነው። የሚያውል የሚያሰድር የ አምክንዮ አቅም ጠፋ፤ አጅንዳ የለም መሼ...