ልጥፎች

ከኦገስት 31, 2018 ልጥፎች በማሳየት ላይ

ነፃነት ከኖረ ድል ከሃሳብ አቅም ይመነጫል።

ምስል
ሃሳብ የማያቋርጥ ጅረት ወይንም ፏፏቴ እንጂ የታቆረ የኩሬ ውሃ አይደለም! „እሱን እግዚአብሄር ስለመረጠው ጌትነቱ እንደ እጁ ሥራ ነውና ባለመድኃኒትን አክብረው።“ መጽሐፈ ሲራክ ምዕራፍ ፴፰ ቁጥር ፩ ከሥርጉተ©ሥላሴ 31.08.2018 ከጭምቷ ሲዊዘርላንድ                                   ትውልድ በፍቅር ማዋህድ የአብይ ሌጋሲ ነው!  ስለዚህም ሊከበርም- ለወደድም ደሊደነቅም ይገባል።  ነገን በፍቅር ማሰብ፤  በእዮባዊነት መቀመር መክሊቱ የእዮር ነው። ተመስገን!  43 ዓመት የተባከነበትም የተተረፈበትም፤ የተጎዳንበትም የተጠቀመንበትም ዘመን ታይቷል - ተፈትሿል። እግዚአብሄር በቃችሁ ሲለን ይህን ዘመን አመጣልን። በዚህ ዘመን ያኮረፉ እንዳሉ ይታወቃል። በዚህ ዘመን ምንም ለውጥ አልመጠም የሚሉ ወገኖችም እንዳሉ ይታወቃል። በዚህ ዘመን የተሻለ ዘመን መጥቷል የሚሉም አሉ።  በርከት ያለነው ደግሞ የተሻለ ሳይሆን የ43 ዓመቱን ዘመን የሚያስንቅ ብሩህ ተስፋን የሰነቀ ነው የምንል ደግሞ አለን። ሰዎች እንደመሆናችን ስለምን ሬድ ሜድ ሃሳብ አልኖረንም ሊባል ግን አይገባም። በሌላ በኩል መልካም ነው በርቱ የምንል አለን፤ መልካም አይደለም የነበረው ይሻል ነበር የሚሉም አሉም። ከነበረውም ከአሁንም ያልሆኑ ወገኖችም አሉ። ወለሌ ገበታ ላይ ያሉም አሉ። ይህም ቢሆን የእናት ሆድ ዥንጉርጉር ስለመሆኑ ስለሚያጠይቅ ተስፋ አስቆራጭ አይደለም።  በሌላ በኩል ደግሞ ፍጽና የሚጠይቁ ሰዎች አሉ፤ ሌሎች ደግሞ ፍጹም የሆነ የተ...