#የኮበሌ መንፈስ ያዘነበላቸው ሚዲያወች ቅኝት። ለእኔ - የአንካራው ሥምምነት።
#የኮበሌ መንፈስ ያዘነበላቸው ሚዲያወች ቅኝት። ለእኔ - የአንካራው ሥምምነት። "የቤትህ ቅናት በላኝ። • https://www.bbc.com/amharic/articles/cly25z39pdpo "ኢትዮጵያ እና ሶማሊያ ከስምምነት የደረሱበት ሰነድ ምን ይዟል?" ሙሉ 11ወር ያልነካካሁት አጀንዳ ነበር። የኢትዮጵያ እና የሱማሌ ላንድ የመግባቢያ ሰነድ #ግጥግጦሽ ። እርግጥ ነው በዚህ ምክንያት የሱማሌ ላንድን ምርጫ ሂደት ከውስጤ ተከታትዬዋለሁኝ። በአንድም በሌላም የእምዬ ጉዳይ ስላለበት። ነባሩ መሪ በተፎካካሪያቸው ተሸንፈዋል። ስለዚህም አዲስ ሁኔታ ይኖራል እራሱ በሱማሌ ላንድ ፖለቲካ። ሱማሌ ላንዶች ጠቅላይ ሚር አብይ በጠረጉላቸው ጎዳና የዓለም ዓቀፍ ሚዲያ ሽፋን በስፋት አግኝተዋል። ስለዚህ + አትርፈዋል። ሰነዱ ሲቀደድ ደግሞ ከስረዋል - ይሆናል። ምን አልባት ዕውቅናውን #ሌላ #አገር ሊደፍረው ይችል ይሆናል። አሁን የሱማሌ ላንድ ህዝብ ግብረ መልሱ ምን ይሆናል ደስታቸውን ስለተነጠቁ??? የሱማሌ ህዝብስ ሲግረጨረጩ ስለባጁ? የኢትዮጵያ ሚዲያወች አብይዝምን የሚደግፋ #ኮበሌ ኮበሌ የሚል ጠረን ያለው ዕርዕስ ሰጥተው እዬዘገቡት ነው። ግርም ብሎኛል። ዕውን ለኢትዮጵያ "ደህንነቱ አስተማማኝ የባህር በር" የአንካራው ስምምነት ያስገኝ ይሆን? ለመሆኑ ሱማሌ የረጋ መንግስታዊ ስርዓት አላትን? አስተማማኝነት ከአንድ አገር የደህንነት አቅም ጋር ስለሚለካካ። አስተማማኝ የመንግሥት ሥርዓት የካርቢያን አገሮች ሲዊዲን፤ ዴንማርክ ኖርወይ፤ ሲዊዘርላንድ ወዘተ ናቸው፤ አውሮፓ እንኳን አሁን በጭንቅም በጦርነትም ላይ ናቸው ነገረ ዩክሬንን ተከትሎ። ፖላንድ፤ ኢስቶንያ፤ ጀርመን ፈረንሳ ይ …… #ግነቱ የሚተናነቅው ሃቅ ም...