ልጥፎች

ከፌብሩዋሪ 20, 2025 ልጥፎች በማሳየት ላይ

#በቁሙ #ቀብር #ላይ #የዋለ #ብትክትክ እንኮሸሽሌ #ዕሳቤ።

ምስል
  #በቁሙ #ቀብር #ላይ #የዋለ #ብትክትክ እንኮሸሽሌ #ዕሳቤ ።   "የቤትህ ቅናት በላኝ።"       Anchor Media ''ጦርነቱ ቢጀመር ደስ ይለኝ ነበር። ...ከዚያን በኋላ የኢትዮጵያ ህዝብ እፎይታን ያገኛል'' ፕ/ር መሀመድ ሀሰን» https://www.youtube.com/watch?v=XotdIljSVEA   ይህቺ አገር ኢትዮጵያ ስንቱን ዝክንትል ዕሳቤ፤ ስንቱን ድሪቶ ምልከታ፤ ስንቱን ስቃይ #ጠሪ ዕሳቤ እንደ ተሸከመች አመላካች ነው። እርእሱን በቁሙ ያለ ተርጓሚ ስታነቡት። ጥገኝነትን ተጠይፋችሁ አመሳጥሩት። የጦርነት ናፍቆት ለእኔ ጭካኔ ነው። በዚህ ጭካኔ ውስጥ ኢትዮጵያዊነትን እስቲ አፈላልጉ? ግን ማህበረ ቅንነት እንዴት ናችሁ? ከሠራተኛ መሪነት፤ ከሊቃውንትም፤ ከዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ሥመጥሩነት፤ ከቀደምት የነፃነት ታጋይነት፤ ከመሪነትም ጎራ የሚመደቡት ባለሁለገብ የልምድ ባለቤቱ ፕሮፌሰር መሐመድ ሃሰን በጦርነት " #እፎይታ " ይገኛል ይሉናል። ማን በሚመራው ጦርነት ብላችሁ ጠይቁልኝ በትህትናም። ሎቱ ስብኃት።    ለእኔ ዝርግ ዕሳቤ ነው። ለእኔ ይህ አንካሳ ዕሳቤ ነው። ፍላጎቱ በግራ ቀኝ ቢኖር እንኳን ይህን ኩፍኝ መንገድ ማበረታት፤ ከጃርታዊው ጦርነትም ተስፋን መጠበቅ እርቃኑን የቆመ ምኞት ነው። እርግጥ ነው አጃቢ ይኖረዋል። ለእሳት ማገዶ እንደሚቀርበው። ግን ለትውልድ ፀር የሆነ አጥፊ ዕሳቤ ነው።   ፕሮፌሰር አንድ ጊዜ አንከር ሚዲያ ላይ "ኢትዮጵያ የሚለው ሥያሜ #ባይስማማን ልንቀይረው ተነጋግረን እንችላለን" ሲሉ #እግዚኦ ብዬ ነበር። ጋዜጠኛ አቶ መሳይ መኮነንም እናቱ ማንነቷን ሊገፍ የሚችል እጮኛ ግን ድውይ ሃሳብ ሲፈልቅ አልሞገተም። ዝም ብሎ አሳለፋቸው። እ...

እኔ መሬት ላይ ተቀምጬ አንተን ሶፋ ላይ አስቀምጬ አስተምርሀለሁ!! ልጆችን የሚያክም ሀኪም ልጆችን መስሎ ቢሰራ !...

ምስል

#ይቅናህ! #ይቅናህ! #ይቅናህ! #ኑርልን #ዋርካ አባቱ

ምስል
  #ይቅናህ ! #ይቅናህ ! #ይቅናህ !      #ዛሬን #ለአንተ #አላህ #ይመርቅልህ ! #ነገንም #አማኑኤል #ለአንተ #ይባርክልህ ! #ዓጤ #አማርኛ #ቋንቋ ፦ #የእማማ #አፍሪካ #ሁነኛ #ነህ ! #የበራህ ፦ #የምታበራ ፤ #የቀደምክ ፤ #የምታስቀድም #ቅኔ #ነህ !   በባዕትህ #ብትገፋም አቅም እና ብቃትህ በዝልቅ ልዕልና በዓለም ተናኝቷል ዛሬን በማግስት ያስጌጣል - ያስውባል- ያብባል።   #ኑርልን #ዋርካ አባቱ የጥንት #የጥዋቱ !   ሥርጉ2025/02/17 ጊዜ ራዲዮሎጂ ነው።

#በተስረከረከ እና #በተሳከረ

  #በተስረከረከ እና #በተሳከረ #ዓላማ እና #ግብ ለድል የሚበቃ፤ የበቃም በድል የተቋጬ ተጋድሎ አይኖርም።  እጅግ በሃዘን ልባችን በሚሰነጥቅ ክስተት ዝምታችን ፍርኃት፤ ወይንም የፖለቲካ ሂደት ብልት ጠፍቶን፤ ወይንም የመሰዋዕትነት አናሳ ሁነት ኑሮብን አይደለም። #ሙግቱም ጠፍቶን አይደለም።  ማራገፋን ኑረንበታል። ትወናውም ሳይገባን ቀርቶ አይደለም። መደበኛ ሥራችን ከዕንባ ጋር ነውና። በሚያረገርግ ምኞት አነሳሽነት የሚካሄድ ማንኛውም ክስተት ይሁን በዘባጣ ፍላጎት እና ፋክክር፤ ንጹኃንን በቋያ አንገርግቦ ከመማገድ ውጪ የሚያስገኜው ተረፈ ዕሴት የለም!!!!!! ህዝባችን በቅጽበታዊ፤ በተለዋዋጭ እና ባልሰከኑ ምኞቶች፦ አቅምን ባልመጠነ ፈሶ በሚለቅም፤ ተለቅሞ በሚፈስ ቅጥአንባሩ በጠፋ ትርምስ ባታሰቃዩት ትለመናላችሁ።  አይገርማችሁም ውድ ማህበረ ቅንነት ማኒፌስቶ ወጣ በተባለ ማግሥት የአመራር ለውጥ ተደረገ? የአማራ ሕዝብ የእነሱ የመለማመጃ ዳንቴል?????!!!!! መጥኔ ለቅኑ የአማራ ህዝብ። ይህን ገመና ተሸክሞ ዛሬም ለሚማገደው።   ሥርጉተ©ሥላሴ Sergute©Selassie 18/02/2025

#መለማመጃ

  #የአማራ #እናት #ማህጸን ፤   #የአማራ #አባት #አብራክ   #የድርጅት #ቅፍቀፋ #መለማመጃ #ዳንቴል #አይደለም !!!!!! ሥርጉትሻ2025/02/19

#ነሽ #ሕይወት

ምስል
  #ነሽ #ሕይወት ግን በእጅጉ #እምታሳዝኝኚ ፦ #ፍጥረት እስኪ ልከትብ ስላአንቺ የእኔ እመቤት ቅኒት - እስቲ በርቺ።     ግን ---- ማገዶ አቅራቢነትሽ ገለማኝ ትብትቡ ጉዞ ይቃኝ ---- አለኝ።   ለሥምየለሽ ባላንጣሽ ለአስመንጥሩ----- ጉደኛሽ በጥቂቱ ---- በጨረፍታ ለአንድአፍታ አወን!---- ለአንድአፍታ በሙግት ትብትቡ ---------ይፍታታ ---- ስለወለላዋ --- ስለታታታ።   እንዲህ ልበል ለአያ እንቶኔ #የምስጥ ጉዞ ምናኔ። አድሪ ለእንቺ መከራ በእጥፍ ድርቡ #አድሪ የተስፋሽ #እምል ቀባሪ።   አንችም ዝም ------ እስከመቼ ---- እኔም ዝም እም!----- #ም ----- እምም። መኖርሽ ሲመዘመዝ ~~~~ የምን ዝም??? አያ እንቶኔ ----- ልለምንህ በእመቤቴ በድንግል በውዷ #ውፅፍተወርቅ እናቴ በአክብሮት ነህና --- ወገኔ ----    ……………እናትህ ሆነህ አታውቅም እና #እባክህ ! #ተዋት ለአማራ እናት --- እባክህን በአማኑኤል ፋታ #ስጣት ። #የወለሌ ድርጅትህ ---- መለማመጃ #ዳንቴል አታድርጋት! አቅምህን አውቀህ #ልቀቃት ። እባክህን?! ---- #ልቀቃት ! ሰርክ ለቋያ -----አትማግዳት የፋንታዚህ መወራረጃ አታድርጋት።   ልቀቃት! -------== እባክህን???? ---- ልቀቃት! የሰርክ የድርጅትህ ማገዶ አታድርጋት። በስል ገብተህ ቅርጥም አድርገህ በላኽው --- ሩብ ዘመናችን ተከዳ በእጅጉ መታመናችን።   እኮ! አያ እንቶኔ ---- የማከብርህ ወገኔ ----- የእኛን አቅም የመጠጥከው ይበቃል፦ በቃኝ! በቃኝ! የፋንታዚህ --- #ብልቃጥ ፦ የዘመን ---- #ምጥ የምድር እንቧይ #ማጥ እልቦሽ ነህና የዕንባ ሰርጥ------ ኩፋኝ #ረ...