ልጥፎች

ከፌብሩወሪ 21, 2019 ልጥፎች በማሳየት ላይ

አዝነን አዝነን እኛም ገርጥተን ሀዘን ሆነን አረፍነው።

ምስል
አዝነን አዝነን እኛም ገርጥተን   ሀዘን ሆነን አረፍነው። „አቤቱ ለምን ርቀህ ቆምክ?“ ምዕራፍ ቁጥር፲፩ ከሥርጉተ © ሥላሴ  Sergute © Selassie  21.02.2019 ከእመ ሲዊዘርላንድ። ግራጫማ መንፈስ ዘመነ ጃዋርውያን እንዲህ አና ብሎ ሲያውጅ አዝንን አዝነን እኛም የጠለሸ ግርጫማ ሀዘን ሆነን አረፍነው ደማችንም ማቅ ለባሽ። ይህ የሆነው ደግሞ ከሐምሌው ዝምታ በኋዋላ የሆነ ነው። ከዚያ በኋዋላ የሚሆነው ሁሉ ብልጭ ድርግም በሚል ናዳና ፈገግታ የዋጀው ነበር። በዛ የዕቀባ፤ የእግዳ ሰሞናት እንጨርሰዋለን ያሉት ነፍስን በፈጣሪ ጥበብ መትረፉ ሌላ ጥርስ አስነክሶ ሌላ ድቅድቅ ትዕይንት ቤተ መንግሥት አካባቢ ያው አፋኙ ቡድን ፈጠረ። አታስታውሱም ውዴቼ አንድ ዓለም አቀፍ የሴቶች ጉባኤ ላይ አኮ የቀድሞዋ ደልዳለ እመቤት ወ/ሮ ሮማን ተስፋዬ ነበር ተገኝተው የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት።  ስለምን ይህ ሊሆን ቻለ ብዬ ሁሉ ጽፌያለሁኝ በወቅቱ … ተወራራሽነት ያላቸው ሰፊ ምልክቶች ነበሩ። ከልቤ ሳዳምጠው በነበረው ጭብጥም ወስኜ የአብይ ዲታ መንፈስ ተጠለፈ ብዬ ጣፍኩኝ። መጣፍ ብቻ አይደለም ሁኔታውን በተደሞ አስቤበትም እንዲያው ለአንድ ዕውቅ የሰብዕዊ መብት ተሟጋች ደውዬ ተናገርኩኝ። በሳምንቱ እሱ እራሱ ኢትዮጵያ መግባቱን ሰማሁኝ። እኔ ኢትዮጵያ ለመግባት ስለመወሰኑ ምንም ዕውቅት አልነበረኝም፤ ግን መተንፈሻ ያጣው፤ ሚስጢር እንዳያወጣ ማዕቀብ የተጠለ በ ት ነፍስ እንዳለ ለሚያውቃቸው አካላት ሹክ እንዲል እና ሁኔታውን በወፍ በር እንዲከተተሉት ነበር ምኞቴ። ምክንያቱም „አክ“ ወሬ በሚል ስጋቱ ብን እንዲል ቅኖች ደግሞ ያን ጥርጣሬ ይታገሉት ስለነበር። የሆነው ግን ያ ዕውነት ነበር። ሁለት ነገር ነበር የተከሰተ