ስለምን ይሆን የኢትዮጵያ ፖለቲካ #አጽናኝነትን እንደ ጦር የሚፈራው?

ስለምን ይሆን የኢትዮጵያ ፖለቲካ #አጽናኝነትን እንደ ጦር የሚፈራው? ለምንስ ይሆን #አይዟችሁ #ባይነት እንደ ወንጀል የሚታዬው? በኢትዮጵያ ፖለቲካ #ሰዋዊነት #አደጋ ውስጥ ነው። ይህ አካሄድ ጨካኞች፦ በጭካኔያቸው ጀግንነት እንዲሰማቸው የሚያደርግ ነው። የኢትዮጵያ ፖለቲካም ለጨካኞች ሽፋን ስለሰጠ የፖለቲካው አውራ መሪ እኔ ነኝ፤ ሥራም ሠርቻለሁ ይላል። ፖለቲካ ሠሪው #ሰው ነው። ፖለቲካ የሚሠራውም #ለሰው እና #ለተፈጥሮ ነው። ስለሆነም #ሰውኛነት ቢያስመሰግን፤ ቢያስከብር እንጂ በኢትዮጵያ የፖለቲካ ህግ #መሳደጂያ ሊሆን አይገባም። የኢትዮጵያ ፖለቲካ ከሰውኛ ማዕቀፍ ውስጥ #ያፈነገጠ ነው። ይህን ማረቅ እና ማሰተካከል ይገባል። #ሃግ ሊባል ይገባል። የኢትዮጵያ ህዝብ በተፈጥሮው አዛኝ፤ ሩህሩህ፤ ደግ እና አጽናኝ ነው። ሃዘኑን በወል በህብራዊነት አስከብሮ የኖረ ህዝብ ነው። ይህን #ጸጋውን #የሚገፍ #አሳቻ ዘመን ላይ ነውና በጥሞና የኢትዮጵያ ህዝብ ሊያስብበት ይገባል። ገዢወቹንም ሊያርማቸው፤ ሊገስፃቸው፤ ሊቆጣቸው ይገባል። ሥርጉትሻ2025/03/26