አገር እናት ናት። እናትም አገር ናት። እናት እና አገር #ትርታ ናቸው ለመኖር።
አገር እናት ናት። እናትም አገር ናት። እናት እና አገር #ትርታ ናቸው ለመኖር።
መኖርም ሆነ አገር እናትነትን #ያከበሩ ሊሆን ይገባል።
እናትነት በኢትዮጵያ ፖለቲካ ከክብሩ በታች እዬታዬ ነው። ትናንትም ዛሬም። ሁልጊዜ መገበር።
እናትነት የዓለም ገዢ #ምህዋር ነው። እናትነት ድንቅ እና ውድ ፀጋ ነው።
እናትነት አስማሚ፤ አረጋጊ፤ አጽናኝ እና ኃላፊነትነትን እና ተጠያቂነትን በተፈጥሮው ልክ ገቢር ላይ የሚያውል #ምሩቅ በረከት ነው።
#እናትነት #የፈጣሪ #የመመረቅ #መግለጫ ነው ማለት እችላለሁኝ።
እናትነት የፈጣሪ እና የተፈጥሮ የሚስጢር #ምስባክ ነው። እናትነት በኢትዮጵያ ፖለቲካ ግን #ሰቀቀን ውስጥ ነው የኖረው።
እናትነት በኢትዮጵያ ፖለቲካ የሃዘን ድንኳን ውስጥ መኖሩ #እንዲከትም የተገደደ ክስተት ነው።
እናትነትን ሳያከብሩ መቅረት የአገርን #ምርቃት ከጉልላቱ ያስነሳል። የፈጣሪ ቁጣን መካችም የለም ከመጣ አፋጣኝ እርማት ሊወሰድ ይገባል። እናትነትን የኢትዮጵያ ፖለቲካ በእጅጉ እዬተዳፈረው ነው።
የኢትዮጵያ እናቶች #ጡታቸውን አሽተው ቆርጠው ከረገሙ ወዮልሽ ኢትዮጵያ ነው። ይህን በጣም ነው እኔ እምፈራው።
እናትነት በኢትዮጵያ ጭቆና ውስጥ ነው። ግፍ እዬተፈጸመበት ነው። የእናቶች ንቅናቄ ከተነሳም አደጋው ዘርፈ ብዙ ነው። ብልጽግና እናትነትን ከጥንስሱ ጀምሮ ፈተና ውስጥ ጥዶታል። ተንገርግቧል - እናትነት።
አስተያየቶች
አስተያየት ይለጥፉ