የኔታዋ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ኢትዮጵያዊ፤ አፍሪካዊ ግሎባላዊት ናት! የኔታዋ ቅድስት ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ዩንቨርስም ናት!
እንኳን ወደ ከበቡሽ ሚዲያ በሰላም መጡልኝ። በስመ አብ ወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አህዱ አምላክ። አሜን። · የኔታዋ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ኢትዮጵያዊ፤ አፍሪካዊ ግሎባላዊት ናት! · የኔታዋ ቅድስት ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ዩንቨርስም ናት! ዕለተ አርብ ማዕዶተ ኢትዮጵያ! በከቡብሽ የቁራሽ እንጀራ ብራና በቢሆነኝ የተብራራ ብራ በሰብለ ሕይወት አዝመራ ለራህብ የሚራራ። „የሰው ልብ መንገድን ያዘጋጃል እግዚአብሔር ግን አካሄዱን ያቃናለታል።“ (ምሳሌ 16 ቁጥር 9) · ዕለተ አርብ ማዕዶተ - ኢትዮጵያ! የኔታዋ አርቶዶክስ ተዋህዶ አገረ ኢትዮጵያን በተፈጥሯዋ ልክ ያበጀች አንቱ ዓይነታ ሃይማኖት ናት። ዕውነት ከተደፈረ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ የተፈጥሯዊነት በቅዱስ መንፈስም ናት። የሰውኛነት ውስጡ ናት። ይህቺ ቤተ- ክርስትያን በጸበሏ ሁሉን በህመም የተንገላቱ ወገኖችን ሁሉ የፈወሰች። በፍቅር ያስተናገደች። የፍቅራዊነት ያጠጣች፤ የሰበከች ሐዋርያም ናት። በጸሎቷ ለሁሉ አጥር ቅጥር ሆነ የኖረች ያኖረች ህልውናም ናት። ዕውቀት አፍልቃ አጽድቃ ያሰበለች ፈርጥ ኃይማኖት ናት። የሥልጣኔም ብሩህ ጎዳናም ናት … ዝማሬዋ፤ ማህሌቷ፤ መልዕክተ ዮኋንሷ፤ ሀሁ ገበታዋ፤ አቡጊዳዋ ለሁሉ እኩል የህሊና መስኖ ሆኖ ሰብዕናን ገንብቷል። አንፆዋልም። ቅድስቷ ቅድስናዋ በማለት ሳይሆን በተግባር ከብራ ያስከበረች የጽረ አርያም ቤተኛም ናት። ቅድስታችን ትምክህትን የናቀች በ...