ልጥፎች

ከኦክቶበር 14, 2026 ልጥፎች በማሳየት ላይ

#ክስተቱ ዓለም ዓቀፍ ንቅናቄ ቢፈጥር ተቋሙ ይጎዳል።

  • የኢትዮጵያ አየር መንገድ እና ቅስም ሰባሪው የአካል እክል የገጠማቸው የአገር ልጆች።    #ክስተቱ ዓለም ዓቀፍ ንቅናቄ ቢፈጥር ተቋሙ ይጎዳል። የኢትዮጵያ አየር መንገድ #ይቅርታ ሊጠይቅ ይገባል። ሰውነትን ሰርዟልና።   "ኃጢያትን የሚከድን ሰው ፍቅርን ይሻል፤ ነገርን የሚደጋግም ግን የተማመኑትን ወዳጆችን ይለያያል" (መጽሐፈ ምሳሌ ምዕራፍ ፲፮ ቁጥር ፱)   https://www.youtube.com/watch?v=7Kb7AdQ0UfE "እናት እና ልጅ ከ21 ዓመት በኋላ | በETH አዝኛለሁ"   #ምዕራፍ ፳።   #ከፋኝ ። እጅግ ከፋኝ።   በኢትዮጵያ አየር መንገድ ላይ ስጽፍ የመጀመሪዬ ነው። የምሳሳለት፤ የምናፍቀው ተቋም ነው። ዛሬ ግን ያዳመጥኩት #ኮሶ ነበር። #አሳንጋላ ነው። ይህን ጹሑፍ ለመፃፍ የተገደድኩበት ሁኔታ #ሰብዕዊነት በኢትዮጵያ #በየነጥብ ጣቢያው ምን ያህል ቀራኒወ ላይ እንዳለ ስለአዳመጥኩ ነው።    ለዛውም አንድ የቀረን የጋራ ቤታችን፤ የወል የመንፈስ ማረፊያችን የኢትዮጵያ አየር መንገድ በራሱ #ዜጋ ላይ የክት እና የዘወትር፤ የውስጥ እና የእዳሪ ልጅ፤ አንዱ በፍቅር ተከብሮ ሲስተናገድ ሌላው ደግሞ ይህን መሰል የተሰወረ #ጫና ፤ ዲስክርምኔሽን ሲፈጸምበት ማድመጥ እጅግ ፈታኙ ገጠመኝ ነው - ለእኔ። ዓለም ዓቀፍ ዕውቅና ያለው፤ በአፍሪካ ተመራጩ የእኛ የምለው ቤታችን በዚህ ልክ #አግላይነት መራራ ገጠመኝ ነው።   በአካሉ እክል ላለበት እኮ የቅድሚያ ቅድሚ ሊሰጥ ሲገባ፤ እግርህን #ጥለህ ግባ ምን ዓይነት ጭካኔ፤ ምን ዓይነት #አረመኔነት እንደሆን አላውቅም። ለዛውም በሴት አስተናጋጅ። ርህርህርህና #ተፍቆ ጭካኔ እንዲህ አና ሲል ማየት እጅግ ...

#አናባቢ (Vowel)። ትዳር መጽሐፍ ነው የሚነበብ።

  #አናባቢ (Vowel)። ትዳር መጽሐፍ ነው የሚነበብ።   "ቤት በጥበብ ይሠራል። በማስተዋል ይጸናል።" (መጽሐፈ ምሳሌ ምዕራፍ ፳፬ ቁጥር ፫።)     #ምዕራፍ ፳።   ይህ እስከ ዛሬ ከሰማሁት ቃለ ምልልስ በላይ ነው። የሚስትነት #ተፈጥሯዊ ማንነት አናባቢ ሆኗል። እንዲህ የቀረብኝን ግን የተመሰጠረ ተራራ ዕጣ እና ጥሪ ውስጡ ያደረገ ሰብዕና ባገኝ ምን ልል እንደምችል አላውቅም።    #የአገላለጽ ዘይቤ።   የንግግር ጥበብ ጥበብ ነው። ጥበቡ በመማርም ይገኛል። ሲታደሉት። ንግግር መማሩ ይሁን የማስተማር ዕድል ያለውም ቢሆን የመናገር አቅም ላይኖረው ይችላል። ርትዑ የመሆንም ጸጋ በዚህ ቃለ - ምልልስ አዳመጥኩ። ንግግር ጥበብ ነው። ጥበቡ በሥልጠና ሲታገዝ ወደ ክህሎት ያድጋል። መስጦኛል የአርቲስት ወ/ሮ አምለሰት የአመላለስ አቅም። አቀራረቡ ግልጽ እና አጭር፤ ግን ውስጥን የማንኳኳት አቅሙ - ገድለኛ። ደርባባ፤ ምራቁን የዋጠ አቅም።    #ሳጉ ብዙ ያስተምራል።    ዕደለኛ ነው ቴዲ። ልኩ የሆንሽ ደልዳላ እመቤት። ጠቅላይ ሚ/ር አብይ አህመድ ወደ ስልጣን ሲመጡ ውጭ ያሉ ቤተሰቦቼ እናቴን በስልክ እንዳገኝ አደረጉ። ስለምፈራ የውጮችንም የአገር ውስጦችንም እናቴን ጨምሮ በስልክ አላገኛቸውም። በውነቱ የመኖር ነፃነታቸው በእኔ ምክንያት መስተጓጎል እንዳይደርስበት በብርቱ እጠነቀቃለሁኝ።    ከባሩድ ምኞት ጋር እኔ የለሁም። ከየትኛውም የፖለቲካ ተቋም ነፃ ነኝ። አንዱም ፈተና ይህው ነው። ግን የኢትዮጵያ ፖለቲካ ብዕርንም ፈሪ ነው። እና ጠንቁ ለቤተሰብ እንዳይደርስ ናፍቆት አገላብጦ እሽት እያደረገኝ ያው ለኢትዮጵያ ተብሎ ቤተሰቦቼን ቀጣሁኝ። ናፍቆትን...