ልጥፎች

ከጃንዩወሪ 24, 2020 ልጥፎች በማሳየት ላይ

ዘመነ - የመቃብር ሥፍራ፤

ምስል
እንኳን ወደ ቀንበጥ ብሎግ በሰላም መጡ። ዘመነ - የመቃብር ሥፍራ፤ እዬሞትክ ጠብቀኝ/ ጠብቂኝ የአብይዝም 50በ60 ያረጠ ፖለቲካ። „እኛ ከጨለማ የተነሳ በሥርዓት መናገር   አንችልምና፤ የምንለውን አስታውቁን።“ (መጽሐፈ እዮብ ምዕራፍ 37 ቁጥር 19) ሥርጉተ©ሥላሴ Seregute©Selassie 24.01.2020 ከጭምቷ ሲዊዘርላንድ መኖርን የነጠቀው የመቃብር ሥፍራ ዘመን ይሁነኝ ተብሎ በቀኝ በግራ ገመናው እንዳይጋለጥ እንክብካቤ እዬተደረገለት ነው። አራስ ቤት ወይንስ ጫጉላ ጊዜ እንበለው ይሆን? በቀዳዳው ሁሉ እንደፍናለን ብለው ተደማሪ ነፍሶች ታከቱ። ብዕሩም ብራናውም፤ ማይኩም መድረኩም „ተስፋ አለን“ እያሉ እልልታውን ያስከንዱታል። ፍልሰፍናውንም ቅብጥ እና ቅልጥ ያደርጉታል። አላዛሯ ኢትዮጵያ ሠርግ ላይ ወይንም ቅልቅል ላይ ወይንም መልስ ላይ ወይንም ግጥግጥ ላይ ያለች ይመስላቸዋል። ከንቱነት! ግን ህሊና እግር ወይንስ እግር ህሊና ቦታ ተለዋውጡ ይሆን? የእኔ እህት ብትሆን? የእኔ ወንድም ቢሆን? የእኔ ልጅ ብትሆን? የእኔ ልጅ ቢሆን ተብሎ እንዴት አይታሰብም? እንደ እኔ ይህ ሰሞን አኮ ብሄራዊ የሃዘን ቀን ሆኖ ሰንደቅ ዓላማ ዝቅ ብሎ የሚወለበለብበት ጊዜ ነበር። ሌሎችም የአስቸኳይ ጊዜ ዓዋጅ መኖር ነበረበት ይላሉ። እነዛ ቀንበጥ እና ሸባላ ልጆቻችን የት እንደ ደረሱ? ምንስ እንደሆኑ እኛ እማናውቀው ነገር የለም። ምን እንደሆኑ ቤተሰብ የሚያውቀው ነገር የለም። ምን ሁኔታ እንደ ተፈጠረ ወላጆች አያውቁም። ወላጆች ልጆቻቸውን ማጣታቸው አልበቃ ብለው ህሊናቸው ደግሞ ይቀጣል፤ ይቀጠቀጣል። አማራነት ግማድ ነው! ዘመዶች ሆኑ እንደ ትውፊታችን ጎረቤቶች፤ ህሊና ያላቸው መምህራን ጭንቅ