ልጥፎች

ከኦክቶበር, 2019 ልጥፎች በማሳየት ላይ

እስክንድር ነጋ እና ኤርሚያስ ለገሰ ከአበበ በለው ጋር - አዲስ ድምጽ በመረጃ ቲቪ | Ethiopia

ምስል

ነፃ ያልወጣችው ሠንደቅ ዓላማ ( ከጸሐፊና ተርጓሚ አቶ መስፍን ማሞ ተሰማ)

ምስል
ነፃ ያልወጣችው ሠንደቅ ዓላማ መስፍን ማሞ ተሰማ አዎ፤ አውሮፓዊው ቅኝ ገዢ ጣሊያን አድዋ ላይ ድል ሆኗል በ 1888 ዓ / ም። በኢትዮጵያና ኢትዮጵያን በሚወክለው ቀስተ ደመናዊ ሠንደቅ ዓላማዋ ላይ ግን ከትውልድ የዘለለ ቂም ቋጥሮ የደማ ልቡን በመዳፉ ደግፎ በተቆረጠው ቋንጃው እያነከሰ አንድ እግሩን ኤርትራ ላይ ልብና ሌላ እግሩን ጣሊያን – አውሮፓ ላይ አድርጎና ጠቅላይ ሚኒስትሩን ፍራንቺስኮ ክሪስፒን ከሥልጣን አባርሮ ድፍን ጣሊያን ሀዘን ተቀመጠ። አርባ ዓመት ሲታመምና ሲያገግም ኖረ። ጣሊያን በኢትዮጵያና በሠንደቋ ላይ ለአርባ ዓመት ያረገዘው ቂም ዱቼንና ፋሽስት ፓርቲን ወለደ። ለጣሊያን ትንሳዔ ኢትዮጵያ መሥዋዕት መሆን አለባት ሲል እነሆ ዱቼ በሮም አደባባይ ተጣራ። ሙሶሎኒ ኢትዮጵያን በመሥዋዕትነት ለተዋረደችው ጣሊያን ትንሳኤ አቀረበ። አውሮፓ አጨበጨበ፤ ቪቫ ዱቼ ሲል ደገፈ። ጥቁር ለባሽ የፋሽስት ጦር ከጣሊያን ጫፍ እስከ ጫፍ ተነቃንቆ ኢትዮጵያን እንበቀላለን ሲል ቃል ገባ። በቫቲካንም ቄስ ተባረከ። ዱቼም ለፋሽስቱ ጦር እንዲህ አለ፤ - ሂዱና ኢትዮጵያን አንበርክኩ፤ የአባቶቻችንንም ውርደት ተበቀሉ፤ አረንጓዴ ቢጫ ቀይ ቀስተ ደመናዊ ሠንደቅ ዓላማዋን አውርዳችሁ እርገጡ፤ አቃጥሉም፤ ዳግም በዚያች ምድር እንዳይውለበለብም አድርጉ፤ ህገወጥ መለያቸው ነውና በሠይፍና በጥይት አግዱ፤ ሠንደቅ ዓላማውን ይዞ ሲያውለበልብም ሆነ ሲምል ለምታገኙት ሁሉ አንዳች ምህረት እንዳይኖራችሁ፤ መፍጀት እስከ