ልጥፎች

ከፌብሩዋሪ 13, 2023 ልጥፎች በማሳየት ላይ
ከፀሐፊ አቶ አሳዬ ደርቤ ያገኜሁት ነው። #እባካችሁ_Share_አድርጉት "ለኦርቶዶክስ ልጆች የተዘጋጀውና አዋሽ አርባ አካባቢ የሚገኘው ምድራዊ ሲዖል!.. ▬▬▬▬▬ እነ ስንታየሁ ቸኮልን ጨምሮ ከአዲስ አበባና ከኦሮሚያ ክልል የታፈሱ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ልጆች የታሠሩት አዋሽ አርባ የማጎሪያ ጣቢያ መሆኑን ስሰማ የሚከተለውን ታሪክ ላጋራችሁ ወደድኩ። አባ ሳሙዔል እስር ቤት ሳለሁ በአዋሽ አርባ የማጎሪያ ጣቢያ ታስረው የከረሙ ከአምስት መቶ በላይ ዜጎችን አግኝቼ ነበር። እኒህንም ዜጎች "ስለ አዋሽ አርባ አውሩኝ እስኪ" ስላቸው ቶርች የተደረገ ሰውነታቸውን እያሻሹ እንዲህ የሚል ተመሳሳይ ማብራሪያ ነበር የሚነግሩኝ። " አዋሽ አርባ የማጎሪያ ጣቢያ ማለት ➔የማታውቀውንና ያልሰራኸውን ወንጀል አጋልጥ" የሚሉ መለዮ ለባሾች ማዕከላዊን የሚያስንቅ አረመኔያዊ ድርጊት የሚፈጽሙበት፤ ➔እንደ ኢሰመኮ እና ኢሰመጎ ያሉ የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ድርጅቶች ከእነ መኖሩም የማያውቁት፤ ➔ቤተሰብ ቀርቶ ሲቪል የለበሰ ሰው የማይታይበት፤ ➔ፍርድ ቤት ሳትቀርብ ከሶስት ወር በላይ ታስረህ የምትቆይበት፤ ➔በ24 ሰዓት ውስጥ አንድ ዳቦና አንድ ኩባያ ውሃ ብቻ በሬሽን መልክ የምታገኝበት፤ ➔የመጸዳጃ ቤት ጥያቄ ስታቀርብ "ፌስታል ላይ ተጠቀም" የሚል መልስ የምታገኝበት፤ ➔ከጸሎት ውጭ ምንም አይነት የሕክምና አገልግሎት የሌለበት፤ እናም እልኻለሁ.... ስንታየሁ ቸኮልን ጨምሮ ከአዲስ አበባና ከኦሮሚያ አካባቢ የታፈሱ አብዛኞቹ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ልጆች የሚጓጓዙት ወደዚያ ምድራዊ ሲዖል ነውና ይሄንን መረጃ ሼር በማድረግ የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ድርጅቶች እንዲደርሱላቸው እናድርግ።"

ከጋዜጠኛ ብርሃኑ ተክለ ያሬድ።

ምስል
  "አድርገህልኛል እና አመሰግንኃለሁኝ።"     መምህር፤ መርጌታ፤ ጋዜጠኛ፤ ርቱዑ፤ ሩህሩህ፤ ጽኑ ወጣት። እሱን የሰጠን አምላክ ይክበር ይመስገን አሜን። ለእናቴ፤ ለክብርቴ፤ ለቅድስት ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ጠቅላይ ቤተክህነት እንደ ልጅነቴ ይህን ባለ ቅብዓ ሽልማት ብትጠቀምበት። ዬተከበረ፤ ዬተደላደለ ቦታ በአማካሪነት ሰጥታ ትውልድ ፋናውን ይከተል ዘንድ ዕድል በሩን ብትከፍት እመኛለሁኝ። ተስፋ ዬእግዚአብሄር ነውና። ተስፋ አደርጋለሁ። እናት ቤተክርስትያኔ የእኔን የትቢያዋን ልጇን መሻት ብታደምጥ። ዛሬ ለደወለችው የደወል ንቅናቄ የዛሬ አራት ዓመት ጽፋዋለች፤ አስተምራዋለች። እናቴ የህልውና አደጋ ላይ ናት ንቁ፤ ትጉ የሚል ሳምንታዊ መርኃ ግብር በድወሏ ድምጽ ብቻ ታቀርብ ዘንድ አስቀድም፤ እጅግም ቀድማ ተናግራለች። ፖለቲከኞች ጥሞና አያውቁም። ላም እረኛ ምን አለ ጉዳያቸው አይደለም። ግን አልበረከቱም። አብሶ አቅምን ማኔጅ በማድረግ አልቦሽ ናቸው። "ኹሉም ነገር የቀናት ጉዳይ ነው። የትኛውም የሴራ ፈትል የትኛውም የተንኮል ጉንጉን መበጣጠሱ አይቀርም!!!ምክንያቱም ሰልፉ የእግዚአብሔር ነው።" ተዋሕዶ #ኢንፈርህ_ሞተ #ሞትን_አንፈራውም ዬሆነ ሆኖ "ዬሚጠላ ሰው ሲያልፍ ብትጠላው ጥቁር አትለብስም ግን ነጭ ለብሰህ አትታይም። " ይገርማል። ዘመን የማይተካው ጋዜጠኛ ጋሼ ሙሉጌታ ሉሌ በድንገት በ2015 እኤአ ስናጣው ስለ እሱ በተሰራ ልዩ ዝግጅት በነጭ ሸሚዝ ያዬሁት አውራ ጋዜጠኛ ነበር። የአውራ ፓርቲ ልሳን። ብፁዑ ወቅዱስ ፓትርያርከ ዘኢትዮጵያ አባታችን ፃድቁ አቡነ መርቀርዮስ በሥጋ ሲለዩን እፎይ ያሉ የሚዲያ ሰወች ሙሽራ ይመስሉ ነበር። ነጭ ለብሰው ነበር ተግባራቸውን የከወኑት፤ ሌላም ሚዲያ ቆራጣ የዕንባ ጠብታ አልነበረም።...

"ዬንጋት ጨለማ ድቅድቅ ነው። ግን አጭር ነው።"

ምስል
"ዬንጋት ጨለማ ድቅድቅ ነው። ግን አጭር ነው።" ትምህርተ አባ ብፁዑ አቡነ ጴጥሮስ። "ወደ እግዚአብሄር ቤት እንሂድ ባሉኝ ጊዜ ደስአለኝ።" አጽናኝ ነው። በከፋኝሰዓት አግኝቼው ያጽናናኝ ነው። በጉነት ቅጣት ዬሚሆንበትን ዘመን ያመሳጥራል። • https://www.youtube.com/watch?v=mc4zFX7mxH0&t=4s «የንጋት ጨለማ መደመጥ ያለበት አጽናኝ ትምህርት || የአባታችን በረከታቸው ይደርብን ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ» ሥርጉተ©ሥላሴ Sergute©Selassie 13/02/2023 ወስብኃት ለእግዚአብሄር። አሜን።  

Es ist eine traurige Geschichte.

Es ist eine traurige Geschichte. • https://www.aljazeera.com/.../whats-behind-the-crisis-in... “What's behind the crisis in the Ethiopian Orthodox Church?” ቅድስቷ እና ዓለም አቀፍ ሚዲያ። "አድርገህልኛል እና አመሰግንኃለሁኝ።" ሥርጉተ©ሥላሴ Sergute©Selassie 13/02/2023  

ትምህርተ ማተብ።

ትምህርተ ማተብ። "1. ሰባቱ አባቶች ሀ. ሰማያዊ አባት እግዚአብሔር ለ. የነብስ አባት ሐ. ወላጅ አባት መ. የክርስትና አባት ሠ. የጡት አባት ረ. የቆብ አባት ሰ. የቀለም አባት 2. ሰባቱ ዲያቆናት ሀ. ቅዱስ እስጢፋኖስ ለ. ቅዱስ ፊልጶስ ሐ. ቅዱስ ጵሮክሮስ መ. ቅዱስ ጢምና ሠ. ቅዱስ ኒቃሮና ረ. ቅዱስ ጳርሜና ሰ. ቅዱስ ኒቆላዎስ 3. ሰባቱ የጌታ ቃላት(እኔ ነኝ) ሀ. የህይወት እንጀራ እኔ ነኝ ለ. የአለም ብርሃን እኔ ነኝ ሐ. እኔ የበጎች በር ነኝ መ. መልካም እረኛ እኔ ነኝ ሠ. ትንሳኤና ህይወት እኔ ነኝ ረ. እኔ መንገድ እና ህይወት ነኝ ሰ. እውነተኛ የወይን ግንድ እኔ ነኝ 4. ሰባቱ ሰማያት ሀ. ጽርሐ አርያም ለ. መንበረ መንግስት ሐ. ሰማይ ውዱድ መ. እየሩሳሌም ሰማያዊት ሠ. ኢዮር ረ. ራማ ሰ. ኤረር 5.ሰባቱ ሊቃነ መላዕክት ሀ. ቅዱስ ሚካኤል ለ. ቅዱስ ገብርኤል ሐ. ቅዱስ ሩፋኤል መ. ቅዱስ ራጉኤል ሠ. ቅዱስ ዑራኤል ረ. ቅዱስ ፋኑኤል ሰ. ቅዱስ ሰቂኤል 6. ሰባቱ አቢያተ ክርስቲያናት ሀ. የኤፌሶን ቤተ ክርስቲያን ለ. የሰርምኔስ ቤተ ክርስቲያን ሐ. የጴርጋሞን ቤተ ክርስቲያን መ. የትያጥሮስ ቤተ ክርስቲያን ሠ. የሴርዴስ ቤተ ክርስቲያን ረ. የፊልድ ልፍልያ ቤተ ክርስቲያን ሰ. የሎዶቅያ ቤተ ክርስቲያን 7. ሰባቱ ተዓምራት ጌታ እየሱስ ክርስቶስ እኛን ለማዳን በመስቀል ላይ በተሰቀለ ጊዜ የተፈፀሙ ተዓምራት ሀ. ፀሐይ ጨልሟል ለ. ጨረቃ ደም ሆነ ሐ. ከዋክብት ረገፉ መ. አለቶች ተሰነጣጠቁ ሠ. መቃብራት ተከፈቱ ረ. ሙታን ተነሱ ሰ. የቤተ መቅደስ መጋረጃ ...