ልጥፎች

ከፌብሩዋሪ 22, 2026 ልጥፎች በማሳየት ላይ

#የ2018ዓ.ም የምርጫ መቅድመ ሙግት ካዳመጥኩት - ትዝብቴ።

ምስል
  #የ2018ዓ .ም የምርጫ መቅድመ ሙግት ካዳመጥኩት - ትዝብቴ።   "እግዚአብሄር በአንድም በሌላም ይናገራል፤ ሰው ግን አያስተውለውም።"   #ምዕራፍ ፲፰።    «የ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ የመጀመሪያው የክርክር መድረክ»  https://www.youtube.com/watch?v=DG6SHFL76_0   ሊንኩን በጥዋቱ ሼር አድርጌዋለሁኝ። በተጨማሪም መቅድመ ውይይት ስለሆነ ልፅፍበት ፈለግሁኝ። በቅድሚያ የሴቶች ተሳትፎ ለፆታ ተዋፆ ብቻ ሳይሆን የኢትዮጵያ ሴቶችን የፖለቲካ ግንዛቤ አቅም ጋር አቻ ሆኖ ሲገኝ ተስፋ ሰጪ ነው። እኔ ለሴቶች ተሳትፎ ልዩ ስስት አለኝ። ሴት ስለሆን ብቻ መድረክ ይሰጠን አይደለም። እእ። አቅም ያላቸው ሴቶች ተመጣጣኝ የፖለቲካ ውክልና ሊሰጣቸው ይገባል ነው የእኔ የትግል ማዕከል። በዘርፋ የፖለቲካ ሊቃናት ሴቶች ከእነሱ #ድፍረት ማነስ ካልሆነ በዘመነ አብይዝም ያለው ሁነት የሚያበረታታ ነው። ብዙ የፖለቲካ ሴት ሊቃናት ወደፊት መጥተዋል። ይህ የውሳኔ አቅም በአወንታዊነት የማየው ነው።    ሌሎችም ተፎካካሪወች ይህን አትራፊ እና ቀና መንገድ በመከተላቸው አመሰግናቸዋለሁኝ።    1) #የመወዳደሪያ ዓርማ።   1.1) የስንዴ ነዶ ባለፈው በስፋት ስለገለጽኩት አልመለስበትም። ነዶ (የጨርቅ ነዶ፤ የእሳር እህል ነዶ፤ የመቃጠል ዓዋጅ፤ የብስጭት መግለጫ) ቃሉ ለማስታወስ ያህል አሻሚ ትርጉም ያለው ስለመሆኑ አጠይቄ ብቻ አልፈዋለሁኝ። (የብልጽግና የምርጫ መወዳደሪያ መለያ ነው የስንዴ ነዶ።)   1.2) ሚዛን። ከገጠር እስከ ከተማ የሁሉንም ትርታ የሚገዛ ነው። (የኢዜማ የምርጫ መወዳደሪያ መለያ ነው ሚዛን።) 1.3) የእጅ ባትሪ። የግል የሆነ፤ ማንም የማያዘ...

መረጃ በወቅቱ ካልቀረበ ይፋድሳል፤ ዕሴቱንም ይቀንሳል፤ በሌላ በኩል አንድ ሥርዓተ #መንግሥት ሥርዓትን መፍቀድ ግዴታው ነው።

ምስል
  መረጃ በወቅቱ ካልቀረበ ይፋድሳል፤ ዕሴቱንም ይቀንሳል፤ በሌላ በኩል አንድ ሥርዓተ #መንግሥት ሥርዓትን መፍቀድ ግዴታው ነው።   "እግዚአብሄር በአንድም በሌላም ይናገራል፤ ሰው ግን አያስተውለውም።"       #ምዕራፍ ፲፰።   #እፍታ ።   የዶክተር ገዱ ምስክርነት እና የጠቅላይ ሚር አብይ አህመድ የመስካሪ ፈላጊ ሂደት ምን ያመሳጥርልናል?   #ተመክሮዬ ።   እንዴት ናችሁ ማህበረ ቅንነት? እኔ አምላኬ ክብሩ ይስፋ ደህና ነኝ።    አንድ ጭብጥ በጣም ሲገርመኝ ሰነበተ። የእኔ የህይወት ተመክሮ የፖለቲካ ፓርቲ ቋሚ እና መደበኛ ሠራተኛ ስለነበርኩኝ ድርጅቴ ኢሠፓ ለተልዕኮ ሲያሰማራኝ ከቡድን መሪ፤ የቡድን ጸሐፊ ጋር ነበር። በተጨማሪም እራሳቸውን ችለው የሚጓዙ ቲሞች ከኖሩም ከፖለቲካ ድርጅቱ በቀጥታ አመራር የሚያገኙ ወደ ተግባር ከመሰማራታቸው በፊት ወጥ የሆነ የተልዕኮ አቅጣጫ ይሰጣቸዋል።   ከተልዕኮ መልስም ሪፖርት ማቅረብ ግዴታቸው ነው። የአቅም ማኔጅመንት የሚታቀደው፤ የሚፈጸመው ከጉዞው #ግብረ መልስ ይሆናል። እኔ የቡድን መሪ ሆንኩኝ፤ ወይንም ሌላ የቡድን መሪ ኖረኝ የማይጓደልበት የዲስፕሊን መርኽ ድርጅቴ ኢሠፓ ነበረው። ለዚህ ነው እኔ የፖለቲካ ፓርቲዬ ኢሠፓ መራራ ስንብት ካደረገ በኋላ በድንግልናዬ የቀጠልኩት። እንኳንስ ፓርቲ የሆነ ተቋም አባልም፤ አካልም መሆን እማልፈቄደው የተፈጠርኩበት ድርጅቴ የፖለቲካ ዲስፕሊኑ፤ ተመክሮው፤ እኛን የቀረጸበት መንገዱ አንቱ ነበር። ከጠቀመ ላጋራችሁ ፈቀድኩኝ።    1) እኛ ለተልዕኮ ስንላክ የተልዕኳችን አጠቃላይ መንፈስ #ይነገረናል ። ሁላችንም በተልዕኳችን ላይ #እኩል ግንዛቤ እንዲኖረን የወል ማብራሪ...

"#ይሁነኝ #ብለን" (ጠቅላይ ሚር አብይ አህመድ) የምርጫ ማዕከላዊ #መርህ #ከቀናው ሙግቱ ተጀምሯል።

ምስል
  " #ይሁነኝ #ብለን " (ጠቅላይ ሚር አብይ አህመድ) የምርጫ ማዕከላዊ #መርህ #ከቀናው ሙግቱ ተጀምሯል።   "አቤቱ ንጹህ ልብ ፍጠርልኝ። አሜን።"   ሰላማዊ የፖለቲካ ተፎካካሪ ፓርቲወች በ2018 ምርጫ ለመሳተፍ ሙሉ ፈቃደኝነት ማሳየታቸው የፖለቲካ #ብልህነት ነው። ተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲወች በስማ በለው ሳይሆን የዕድሉ ባለቤት ሆነው ዕድላቸውን #ሳያፈሱ በዕድሉ ሊጠቀሙ ይገባል። ይህ ሂደት ፖለቲካዊ #ብልህነትም ነው። ሰላማዊ ትግል ለመረጠ አንድ የፖለቲካ ድርጅት ዓላማ እና ግቡን #ለማስተዋወቅ ፤ #ከቀናው #ለመፈጸም እና ለማስፈጸም ብቸኛ ጎዳናው #ምርጫ ብቻ ነው።   በምርጫ መሳተፍ ብዙ በጣም ብዙ ትርፎች ሲኖሩ እንዲህ በመንግሥት ሚዲያ #ዕድሉን ሲያገኙ የማኒፌስቷቸውን ጭብጥ #ቀለል ባለ አገላለጽ ለኢትዮጵያ ህዝብ ማቅረብ ይችላሉ። ደጋፊወቻቸው ያነቃቃሉ። የፖለቲካ ባህል ይዳብራል።    ለተፎካካሪ የፖለቲካ ሊቃናት ይሁን ለገዢው ብልጽግና ሊቃናት የልምድ፤ የተመክሮ፤ የንግግር ጥበብ ባህል የሚማሩበት፤ የሚያሳድጉበት ነው። በመሸነፍ ውስጥ ማሸነፍ፤ በማሸነፍ ውስጥ መሸነፍ እንዳለ ዕውቅና ሊሰጡት ይገባል።   ገዢው ፓርቲ ብልጽግና ማዋከብ፤ ጫና ማድረግ፤ ማሰር መፍታት፤ ማስፈራራት አይኖርበትም። በተለይ የታችኛው አካላቱ ይህን መንገድ አካላቱ ስለሚከተሉ " #ይሁነኝ " ብለን መርህ ይከበር ዘንድ ክትትል ሊደረግበት ይገባል።    ብልጽግና በማየው ልክ #ምንም የሚያሰጋው ነገር ያለ አይመስለኝም። 50+ የማግኜት ዕድሉ ሰፊ ነው። ስለዚህም በሆደ ሰፊነት ምርጫው ካለምንም ጫና ለውጤት ይበቃ ዘንድ #ትዕግሥቱን #ሥራ ላይ ሊውል ይገባል ባይ ነኝ።   ከምርጫ ጋራ በተ...