"#ይሁነኝ #ብለን" (ጠቅላይ ሚር አብይ አህመድ) የምርጫ ማዕከላዊ #መርህ #ከቀናው ሙግቱ ተጀምሯል።
"አቤቱ ንጹህ ልብ ፍጠርልኝ። አሜን።"
ሰላማዊ የፖለቲካ ተፎካካሪ ፓርቲወች በ2018 ምርጫ ለመሳተፍ ሙሉ ፈቃደኝነት ማሳየታቸው የፖለቲካ #ብልህነት ነው። ተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲወች በስማ በለው ሳይሆን የዕድሉ ባለቤት ሆነው ዕድላቸውን #ሳያፈሱ በዕድሉ ሊጠቀሙ ይገባል። ይህ ሂደት ፖለቲካዊ #ብልህነትም ነው። ሰላማዊ ትግል ለመረጠ አንድ የፖለቲካ ድርጅት ዓላማ እና ግቡን #ለማስተዋወቅ፤ #ከቀናው #ለመፈጸም እና ለማስፈጸም ብቸኛ ጎዳናው #ምርጫ ብቻ ነው።
በምርጫ መሳተፍ ብዙ በጣም ብዙ ትርፎች ሲኖሩ እንዲህ በመንግሥት ሚዲያ #ዕድሉን ሲያገኙ የማኒፌስቷቸውን ጭብጥ #ቀለል ባለ አገላለጽ ለኢትዮጵያ ህዝብ ማቅረብ ይችላሉ። ደጋፊወቻቸው ያነቃቃሉ። የፖለቲካ ባህል ይዳብራል።
ለተፎካካሪ የፖለቲካ ሊቃናት ይሁን ለገዢው ብልጽግና ሊቃናት የልምድ፤ የተመክሮ፤ የንግግር ጥበብ ባህል የሚማሩበት፤ የሚያሳድጉበት ነው። በመሸነፍ ውስጥ ማሸነፍ፤ በማሸነፍ ውስጥ መሸነፍ እንዳለ ዕውቅና ሊሰጡት ይገባል።
ገዢው ፓርቲ ብልጽግና ማዋከብ፤ ጫና ማድረግ፤ ማሰር መፍታት፤ ማስፈራራት አይኖርበትም። በተለይ የታችኛው አካላቱ ይህን መንገድ አካላቱ ስለሚከተሉ "#ይሁነኝ" ብለን መርህ ይከበር ዘንድ ክትትል ሊደረግበት ይገባል።
ብልጽግና በማየው ልክ #ምንም የሚያሰጋው ነገር ያለ አይመስለኝም። 50+ የማግኜት ዕድሉ ሰፊ ነው። ስለዚህም በሆደ ሰፊነት ምርጫው ካለምንም ጫና ለውጤት ይበቃ ዘንድ #ትዕግሥቱን #ሥራ ላይ ሊውል ይገባል ባይ ነኝ።
ከምርጫ ጋራ በተያያዘ አንድም ኢትዮጵያዊ ዜጋ ምንም ዓይነት ጉዳት ሊደርስበት አይገባም። የጠቅላይ ሚር አብይ አህመድ ቃል "#ይሁነኝ ብለን" ዕውን መሆን መቻል ይኖርበታል።
የማከብራችሁ የአገሬ ልጆች ይህ #መቅድሙ ስለሆነ ነው ሼር ያደረጉት። ቀጣይ ውይይቶችን እነንተው ተከታተሉት። ማንኛውም ሰው፤ የትኛውም ተቋም ዕድል ማፍሰስ ሊጠቅመው አለመቻሉን አበክሬ እየገለጽኩ ቸር ሰንበት ይሆንላችሁ ዘንድ እመኛለሁኝ።
ቸር አስበን፤ ቸር እንሁን። አሜን።
ቅን አስበን፤ ቀና እንሁን። አሜን።
መልካም ሰንበት። አሜን።
ሥርጉተ©ሥላሴ
Sergute©Selassie
22/02/2026
ዕውነት ወጌሻ አያስፈልገውም።
ጊዜ ራዲዮሎጂ ነው።

አስተያየቶች
አስተያየት ይለጥፉ