ልጥፎች
ከጁን 21, 2019 ልጥፎች በማሳየት ላይ
መጸሐፍቶቼ ልጆቼም ነፃነቶቼም ናቸው!
- አገናኝ አግኝ
- ፌስቡክ
- X
- ኢሜይል
- ሌሎች መተግበሪያዎች
"የሰው ልብ መንገድን ያዘጋጃል፤ እግዚአብሔር ግን አካሄዱን ያቃናለታል" መጽሐፈ ምሳሌ ፲፮ ቁጥር፱ ተስፋ ይመጣል ተስፋም ይሄዳል ተስፋም ያነጉዳል ተስፋም ይክሳል ... አንድ ቀን ... ይጠበቃል! እንኳን በደህና መጡልኝ መጸሐፍቶቼ ልጆቼም ነፃነቶቼም ናቸው! ልጆችን መንከባከብ ደግሞ የማህበረሰቡ ተግባር ነው። ተስፋችንም በፖለቲካ ሊሂቃኑ ሳይሆን በማህበረሰባችን ብቻ ነው! v እፍታ። የኔዎቹ የኔታዎቼ እንዴት ናችሁ የአገሬ ልጆች? ደህና ናችሁ ወይ? ማህበረሰባችን በዬአካባቢው በመንፈስ የታሠሩትን ልጆቹን ማስፈታት ይኖርበታል። ስደት የምንኖረው ባለመክሊት ልጆቹም በስውር ካቴና ነው የባጀነው ውጭ አገር። አብሶ አማራነት ቀራንዮ ነው ። ማህበረሰባችንም እራሱን በሽንገላ ሳይስከበብ ነጥሮ መውጣት ይኖርበታል። ስለሆነም ለድጋሚ ዕስርም ራሱን ማሰናዳት እንደሌለበት አበክሬ አስገነዝባለሁኝ። ታገሽነቱ በተግባር ይመሳጠር። አሁን ያለው የአገር ውስጥም የውጭ ጭቆና ዓይነት እና ስልትና የጭካኔ ተመክሮ የጫጉላ ሽርሽር እንዴት ሁለቱን አቀናጅቶ ጭቆናን ሉላዊ በማድረግ ንቁ፤ ትጉህ ኢትዮጵውያንን በሁሉም አቅጣጫ ማፈን እና ሰላ ማቸውን ማስጣት ይቻላል ነው ምክክሩ። ይህ ስለላ እሰከ አውሮፓ ህብረትም ይዘልቃል። ውሉም ጋብቻውም ይኼው ነው። ሞጋች ማህበረሰብ አይፈለግም። ግን ስንቱን አግልለው፤ ስንቱን ከጫዋታ ውጭ አድርገው እንደሚዘልቁት ወፊቱ ትጠዬቅ። ግሎባላይዜሽኑን በኢጎ አፍነው ማስቀረት ከቻሉ ይሞክሩት። ጥቂት ሰዎች ህይወታቸውን ሊያጡ ይችላሉ ... ግን እልፎችን ያፈራሉ ... ስለሆነም የአፈና...