ልጥፎች

ከኦክቶበር 27, 2025 ልጥፎች በማሳየት ላይ

የኢትዮጵያ ሴቶችን የደህንነት ዋስትና የሚያስጠብቅ ክብራቸውን የሚያስጠብቅ #አዲስ #ህግ #በእናት #ሥም ለኖረችው ኢትዮጵያ ያስፈልጋታል።

ምስል
  የኢትዮጵያ ሴቶችን የደህንነት ዋስትና የሚያስጠብቅ ክብራቸውን የሚያስጠብቅ #አዲስ #ህግ #በእናት #ሥም ለኖረችው ኢትዮጵያ ያስፈልጋታል።   የመጀመሪያዋ #ትምህርት ቤት እናት ናት። የመጀመሪያዋ የፊደል ገበታም እናት ናት።    "አቤቱ ንጹህ ልብ ፍጠርልኝ።" አሜን።        ምዕራፍ ፲፯   #ጠብታ ።   እንዴት ሰነበታችሁ የቅንነት ክብረቶች? እኔ አምላኬ ክብሩ ይስፋ ደህና ነኝ። የኢትዮጵያ ሴቶች የኢትዮጵያዊነት ጽንሰ ሃሳብ ከተጸነሰ ጀምሮ የጎላውን ድርብ ድርሻ የተወጡ ጀግና የማህበረሰብ አካሎች ናቸው። በዲፕሎማሲው ዘርፍም ቀደምት ናቸው። በአገር መሪነትም መቅድም ናቸው።   የሆነ ሆኖ የሴቶች እናትነት ጸጋ ለማናቸውም ችግር የመፍቻ ቁልፍ ነው። ይህ ደግሞ ሰው - ሰራሽ፤ ጊዜ - ሠራሽ፤ ሥልጣን - ሠራሽ፤ ስልጣኔ - ሠራሽ፤ ዘመን - ሠራሽ ጉዳይ አይደለም። በፈጣሪ አምላካቸው/ በአላሃቸው ተባርኮ እና ተቀድሶ የተሰጣቸው ሰማያዊ ምርቃታቸው ነው።   የእናቶች ምርቃታቸው እንከን የለሽ ነው። ምርቃታቸው ጊዜ የማይሽረው ዘመን የማያወይበው ነው። ሴቶች አገቡም // አላገቡም፤ ወለዱም // አልወለደሙ ሴቶች የተፈጠሩበት ታላቅ ሚስጢር #እናትነት ነው። እናታዊነት ከእነ ሙሉ ጸጋው በእያንዳንዷ አንስት ውስጥ ተለብጦ ሳይሆን ተዋህዶ ማንነቷን አብርቶ እና አፍክቶ እንዲገኝ የሚያደርግ ንጥረ ነገር ነው። የሴቶች የማንነት ገላጭ ምስክራቸው እናታዊ ጸጋቸው ነው።    #እናታዊነት ።   * እናታዊነት ርህርህና ነው። ** እናታዊነት አዛኝነት ነው። *** እናታዊነት አጽናኝነት ነው። **** እናታዊነት አይዟችሁባይነት ነው። ***** እናታዊነት ቅን...