መነቀስ>>>>>> እኛበእኛ።
እንኳን ደህና መጡልኝ። „ተነሡ፤ መልዕከተኛ ወደ አህዛብ ተልኮ፣ --- ተነሡ፤ በላይዋ በሰልፍ እንነሣ ብሎአል።“ ትንቢተ አብድዩ ምዕራፍ ፩ ቁጥር ፩ መነቀስ >>>>>> . እኛበእኛ። ከሥርጉተ © ሥላሴ Sergute©Selassie 06.04.2019 ከእመ ዝምታ ሲዊዘርላንድ። እንዴት ናችሁ የኔዎቹ ? ደህና ናችሁ ወይ ? መነቀስ ዘመኑን የሚገልጠው ይመስለኛል። ዛሬ የረባ ነገር ሳልሰራ ነው የዋልኩት። ዝም ብዬ ስለመነቀስ እኛበእኛ ሳስበው፤ ሳስበው አልገፋ ሲለኝ ነው ወደ ብራናዬ መጣሁት። ዝም ብዬ ሳስበው ይህ ከጣና ኬኛ ጀምሮ ያለውን ሁነት ፊልም ልስራው ቢባል ምን እና ምን ሊሆን እንደሚችል የ ጭብጡ ታሬና ቁንጮ ቁጭ አድርጌ አወያዬሁት። እሱ ጥሩ አድማጭ እኔ ደግሞ ተናጋሪ ሆኜ፤ … የዛሬን አያድርገው እንጂ የወጣልኝ ተናጋሪ ነበርኩኝ … ጥሩ አድምጭም ... የሁሉም ወረርሽ እንዲህ ሊሆን ሁሉም ሊደርሰው ማለቴ ነው ዛሬ ላይ እኔ ሰለባው ነበርኩኝ የመነቀስ … አሳዛኙ ቀጣይነቱ ቢሆን ዛሬ የእኔ የኖርኩበትን ሰቀቀን የሚጋሩ የእውነት አርበኞች የግንባር ሥጋዎች በርከት ብለዋል መታዬታቸው ነው፤ ቀደም ባለው ጊዜ ነጠል ብለው ቢወጡም ሸፋኝ፤ ጋራጅ፤ አለን የሚሉት ጥግ ነበራቸው፤ ዛሬ ግን ያው የእኔ ቢጤ ነው የሆኑት ...ብዬ አስባለሁኝ … ዘመድ ተገኜ እንደማለት ... · እምታን በነፍሰጡር እይታ … ያጠፋነውን...