ልጥፎች

ከኤፕሪል 9, 2021 ልጥፎች በማሳየት ላይ

የኢትዮጵያ ዕለቶች ዕንባ እዬለቀሙ። 09 04 2021

ምስል

ኢትዮጵያዊነት ምንጩና አገነባቡ ከሃሳብ በላይ ነው።

ምስል
  እንኳን ወደ ከበቡሽ ብሎግ በሰላም መጡልኝ።   ዕለተ አርብ ማዕዶተ - ኢትዮጵያ በከበቡሽ የቁራሽ እንጀራ ብራና በቢሆነኝ የተብራራ ብራ በሰብለ ሕይወት አዝመራ ለራህብ የሚራራ።   ኢትዮጵያዊነት ምንጩና አገነባቡ ከሃሳብ በላይ ነው። ጥፈተኛው ማን ነው?   „ከቀና ህግ ወጥተን ሳትን“ (መጽሐፈ ጥበብ ምዕራፍ ፭ ቁጥር ፮) ·        እፍታ። ·          ማዕዶተ ኢትዮጵያዊ። ኢትዮጵያዊነት ዘለግ ያለ ፍልስፍና ነውና አንዲት ነቁጥ አንስቼ ሃሳቤ ረዘሟል። እምጽፈው ለቅኖች፤ ለገራገሮች ስለሆነ ብዙም ጭንቅ የለብኝም ዘለግ ያለ ስለመሆኑ። እኔን ሽተው ለሚመጡ ደጎቼ ውስጤን ገልጬ ስጽፍም ሰቀቀን የለብኝም እንደ ማለት። ግልጽ እና ቀጥተኛ ሴትም ነኝ። ሰው ጫካ አይደለም እና። ·        መንፈስ!   እንዴት ናችሁ የኔዎቹ? ደህና ናችሁ ወይ ?  ኢትዮጵያ ሻሸመኔ፤ ኢትዮጵያ ቡራዩ፤ ኢትዮጵያ ለገጣፎ ለገዳዲ፤ ኢትዮጵያ ወለጋ፤ ኢትዮጵያ ሙሉ ኦሮምያ፤ ኢትዮጵያ ቤንሻንጉል ጉምዝ፤ ኢትዮጵያ ደቡብ፤ ኢትዮጵያ ከሚሴ - አጣዬ - ማጀቴ - ደራ፤ ኢትዮጵያ ማህል ጎንደር፤ ኢትዮጵያ ትግራይም፤ ኢትዮጵያ አፋር እና ሱማሌም ፍጥጫ ላይ ነው የባጁት፤ ያሉት፤ የሰው እልቂት ምድሪቱን ከቧታል። ደሙም አጉርፏል።    ገና ውጥን ላይ እያለ ጭካኔው ቁጣ አልነበረም ቀጠለ። የቆዬ ስለመሆኑ አይደለም ጉዳዩ ዛሬም   የኦሮሙማ ባጀቱ ሰው መግደል ነው፤ ሬሳ መቁጠር፤ ሰኔል እና ቹቻ በቦንዳ ማከ...