ሚስጢረ - ባቲካን። • ዕርዕሱ የእኔ ዘገባው የBBC አማርኛው ክፍል።
ሚስጢረ - ባቲካን። • ዕርዕሱ የእኔ ዘገባው የBBC አማርኛው ክፍል። https://www.bbc.com/amharic/articles/cq80g5ene7jo «ቀጣዩ የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን ሊቀ ጳጳስ ከአፍሪካ ሊመረጡ ይችላሉ?» 24 ሚያዚያ 2025, 07:00 EAT «ቀጣዩን የሮማ ሊቀ ጳጳስ ለመምረጥ መስፈርቱ የካቶሊክ ቤተክርስቲያን በፍጥነት እየተስፋፋች ያለችበት አካባቢ ከሆነ በእርግጠኝነት ከአፍሪካ ሊሆን እንደሚችል መተንበይ ይችላል። ከየትኛውም የዓለም ክፍል በተለየ በአፍሪካ የካቶሊክ እምነቱ ተከታዮች ቁጥር በከፍተኛ መጠን እያደገ ነው። እየጨመረ ያለው የእምነቱ ተከታዮች ቁጥር በመላው ዓለም ካሉ አህጉራት አንጻር ሲወዳደር ከግማሽ በላይ የሚሆነው እድገት የተመዘገበው በአፍሪካ ነው። ከዚህ ቀደም ከ1500 ዓመት በፊት አፍሪካዊ መሆናቸው የሚታመነው የቤተ ክርስቲያኒቱ ጳጳስ ገላሲያስ ቀዳማዊ ቤተ ክርስቲያኒቱን በርዕሳነ ሊቀ ጳጳስነት አገልግለዋል። የሮማ ካቶሊክ ቤተ ክርስቲያንን በቀጣይነት የሚመራውን አባት የሚመርጡት ካርዲናሎች ሲገናኙ ውሳኔያቸውን ይህ እውነታ ተጽዕኖ ያሳድርበት ይሆን? ናይጄሪያዊው ካህን አባ ስታን ቹ ኢሎ አመራሩ ዓለም አቀፍ ምዕመኑን የሚያንፀባርቅ መሆን እንዳለበት በመግለጽ "አፍሪካዊ ጳጳስ ቢኖር በጣም ትልቅ ነገር ነው" ይላሉ። አባ ስታን ቺ ኢሎ ካርዲናሎቹ ከፍተኛ ተቀባይነት እንዲሁም "ተሰሚነት ያለውን ጳጳስ" ሊመርጡ እንደሚችሉ ተናግረዋል። "ተግዳሮቱ በቫቲካን በአሁኑ ወቅት ከፍተኛ ሹመት ላይ ያለ አፍሪካዊ ካርዲናል የለም፤ ያ እንቅፋት መሆኑ አይቀርም" ይላሉ። "ጳጳስ ሆነው ለመሾም ብቃት ያላቸው፣ በዓለም የካቶሊክ ማኅበረሰብ ዘንድ ተሰሚነት ያ...