#የአንከር ሚዲያ ሰሞናተ - ሙግቱ ይበል ያሰኛል። ሚዛን ግን ይጠይቃል ሰላሙ ለአማራ እናትስ ይላል።
#የአንከር ሚዲያ ሰሞናተ - ሙግቱ ይበል ያሰኛል። ሚዛን ግን ይጠይቃል ሰላሙ ለአማራ እናትስ ይላል። "የቤትህ ቅናት በላኝ።" ትናንት ጋዜጠኛ መሳይ መኮነን ከአቶ ሚኪ ተስፋዬ ጋር ቃለምልልስ ነበረው። ሙሁራን አቅርቦ ሲሟገት እከታተለዋለሁኝ። ተደማጭም ጋዜጠኛ ነው። እንግዶቹን ወደ እሱ ምልከታ ለማምጣት የሚያደርገው ፍልሚያም የጉድ ነው። ድሮ ድሮ በብዙ እሞግተው ነበር። አሁን ሙግት አቆሚያለሁኝ። እሚገርመኝን አመክንዮ ግን ማቅረብ ግድ ይሆናል። ከተደመጠ #ስርክርክ የሚሉ ዕሳቤወችን ማጽዳት ይገባል። ጋዜጠኛ መሳይ መኮነን የትግል ሚዲያ ክፍሉ ይመስለኛል። ዝንባሌውም ወደዛ ነው። የሆነ ሆኖ ሰሞኑን ግን እሱን እራሱ በራሱ ሚዲያ የሚሞግቱት በርክተዋል። በተራው እዬተሞገተ ነው። ይህ ሸጋ ገጠመኝ ነው። የጠበቃ አርበኛ አስረስን ሙግትም አዳምጫለሁኝ። ጠበቃው ቀላል አልነበረም። ፍላጎቱን አስከብሮ ነበር ውይይቱ የተጠናቀቀው - በእኔ ሚዛን አርበኛ አስረሱ አሸንፏል ባይ ነኝ።።። ብቁ ወጣት ነው ጠበቃ አስረስ። ለህይወቱ ግን #እሳሳለታለሁኝ ። አይደለም ለአማራ ለኢትዮጵያም የሚጠቅም፦ እራሱን በአግባቡ መግለጽ የሚችል ወጣት ነው። በሚያምንበት ሃሳብ የኢትዮጵያ የፖለቲካ ማሳ ቀለመ #ህብር ያደርገዋል እና። ሰላሙ ቢገኝ። ትናንትም አቶ ሚኪ ተስፋዬም እንደ ጉድ ነበር የሞገቱት ጋዜጠኛ መሳይ መኮነንን። ኢትዮጵያ ውስጥ በዜግነት ፖለቲካ ላይ የሚሠራ #ሰላማዊ ታጋይ ይህን ያህል አቅም ያለው አለን ብያለሁኝ። ሚዛን ላይ ሆነው የሚያምኑበትን ፋክት አላስነካም ብለው በድፍረት፤ በእርግጠኝነት ወሳኝ በሆኑ አመክንዮወች ጋዜጠኛው እስኪበቃው ተሞግቷል። አልተበገሩለትም። ደስ የሚል ፍልሚያ ነበር። ...