የሱማሌው ችግር የተፈታበት መንገድ እንደገና ታጥቦ ጭቃ - ዳጥ ላይ? ህም!
ጭጎጎታማ ዳመና። „ሰማይ ጽድቁን ይናገራሉ፤ እግዚአብሄር ፈራጅ ነውና።“ መዝሙር ፵፱ ቁጥር ፲፮ ከሥርጉተ©ሥላሴ Sergute©Selassie 23.01.2019 ከእመ ዝምታ። ጤናይስጥልኝ ውዶቼ እንዴት ናችሁ? ደህና ናችሁ ወይ። ዛሬ ብራ ነው። ብራ እወዳለሁኝ። በዛ ሰሞን ዘሃበሻ ስለ ሰብዕዊ መብት ጽኑ ተሟጋቹ አቶ ሙስጡፋ ዑመር ከሥልጣን የመልቀቅ ጥያቄ ሹክ ብሎን ነበር። መርዶ ነበር ለእኔ። ድክም እያለኝ ነበር ያዳመጥኩት። መረጃው ቀዝቃዛ ነበር ስቀበለው። ብርድ ብርድ ብሎኝም ነበር። ዛሬ ደግሞ አንድ አጭር ውይይት ከአንድአፍታ አዳመጥኩኝ። እጅግ እማከብራቸው አክቲቢስት አቶ ጀማል ዲሪዬ ጋር የተደረገ ቃለ ምልልስ ነው። እሳቸው የፕሬዚዳንቱ የህግ እና የሰባዕዊ መብት አማካሪ መሆናቸው እጅግ ድንቅ ነገር ነው። በዚህ ደስ ብሎኛል። ግን ሊሰሩበት የሚገባው እርግጠኝነት ድጋፍ አልባ ነው። ብረት መዝጊያ የሆነ መንፈስ ያስፈልጋቸዋል። የሱማሌ ጉዳይ የተፈታበት መንገድ ከሁሉም አገር ውስጥ እርምጃዎች እጅግ የላቀው ነበር ማለት እችላለሁኝ። ታጥቦ ጭቃ እንዳይሆን ግን ስጋት አይሏል። በውጭ ስንመለከተው የኢትዮጵያ ኤርትራን ጉዳይ ጉልሁ ማለት እንደምችለው ነበር ያን እርምጃ እኔ ያዬሁት የአቶ አብዲ ኢሌ በቁጥጥር ሥር መዋል እና የአቶ ሙስጡፋ ዑመር ወደ ሥልጣን መምጣት የታምር ያህል ነበር የተመለከቱከት፤ ተከታታይ ጹሑፎችንም በአጽህኖት ጽፌ ነበር። ለዛውም ማንም ያን ጊዜ ከቁብ የቆጠረው ባነበረበት ጊዜ ነው እኔ ተደሞውን ያስኬድኩት። አንድ ሰው የሰብዕዊ መብት ተሟጋች መሆኑ በተለይ በሉላዊ ዓለም ለመስራት መታደሉ የተለዬ ጸጋ ነው ያን ወደ ኢትዮጵያ ኢንቤስት ለማድረግ መታሰቡ ራሱ እንኳንስ እርምጃው...