የጃርት ጉባኤ ርደት። Poesie By Sergute Selassie Der Mensch wurde zum Guten gesc...
የጃርት ጉባኤ ርደት *** ባድም በጃርት ተሰቅዛ ... በአረማሞ አራሙቻ ናውዛ። እህህን ሰንቃ ደንዝዛ ... ሰቀቀን ታጥቃ አርግዛ። በ’ሬት ጨጎጎት ተደልዛ ... መቀነት በእሾህ ተገንዛ ... ቁም ስቅሏን አዬች - ይህው በልዛ። ጃርተ - ምርት፣ እሾህ ... ፍጥረተ - ነገሯ፣ ውጋት። ... በበቀል ተዋቅራ በደም ተቋድሳ በደጋን ታምሳ ተደቁሳ። እሾህ አዘራች መልሳ .. የጃርት ገላ መላልሳ። ህልም ራዕዩ ምልግልግ የላንቁሶ ውሃ ዝልግልግ። ጃርተ- ልብ፣ የእሾህ ልግ የአሜኬላ የቋሳ ድግዳግ። ጃርትስ አሰኛት የበቀል ብቅል የአብሾ ጠላ ዝልል። ቋቱ የማያውቅ ግልግል የጃርት ህሊና የውጋት ግልገል ... ... ሰባራ ገል። እሾህስ አልቦ የለም ጃርት ከዘረ እሾህ የለም ምርት። የጠቀራ ናስ ሃሞት ዙሪያ - ገባው፣ ማት ... ... ህልፈት የሐገር ቅብረት። አንተ አለህ እና በቤትህ ትሰማለህም ታያለህም የጃርተን-ትእቢት፤... የቀን ጥሰትን የበቀል አምላክ አትለፋት የሕዝብን ዕንባ ህማማት ... እ!-እ!-እ!-እ!-እ!-እ!-እ!-እ-! እም-እ-እ-እእ ግንቦት 20 ቀን 2000 ዓ.ም አንደልፊንገን-ሲዊዘርላንድ