ልጥፎች

ከኖቬምበር 7, 2024 ልጥፎች በማሳየት ላይ

የፍቅርን ተፈጥሮ የሚያበረታቱ መዳረሻወች። Zugang, die die Natur der Liebe fördern.

ምስል

«በአማራ ክልል አራት ካምፖች “ለጅምላ ማሰሪያነት” መዋላቸውን አምነስቲ አስታወቀ

  https://www.bbc.com/amharic/articles/ce9gxlvyyzro «በአማራ ክልል አራት ካምፖች “ ለጅምላ ማሰሪያነት ” መዋላቸውን አምነስቲ አስታወቀ በአማራ ክልል ለአንድ ወር በዘለቀው “ የዘፈቀደ እስር ” የተያዙ “ በሺዎች የሚቆጠሩ ” ነዋሪዎች በዳንግላ፣ ኮምቦልቻ እና ሸዋ ሮቢት ከተሞች እንዲሁም በጭልጋ ወረዳ በሚገኙ ጊዜያዊ የእስር ካምፖች ውስጥ እንደሚገኙ አምነስቲ ኢንተርናሽናል አስታወቀ። አምነስቲ፤ “ ኢትዮጵያ ለአገራዊ፣ ለአህጉራዊና ለዓለም አቀፋዊ የሰብአዊ መብት ግዴታዎች ግድ የለሽ ወደመሆን አዲስ ምዕራፍ ገብታለች ” ሲል ወቅሷል። ዓለም አቀፉ የሰብአዊ መብት ተሟጋች ተቋም ይህንን ያለው ካለፈው መስከረም ወር ጀምሮ በአማራ ክልል እየተፈጸመ ያለውን “ የዘፈቀደ እስር ” በተመለከተ ትናንት ረቡዕ ጥቅምት 27 ፤ 2017 ዓ . ም . ለሁለተኛ ጊዜ ባወጣው መግለጫው ነው። ተቋሙ፤ በክልሉ እየተፈጸመ ያለውን እስር እና የእስረኞች አያያዝ በተመለከተ ከእስር ካምፖች የወጡ ሰዎችን ጨምሮ ለጉዳዩ ቅርበት ያላቸውን አካላት እንዳነጋገረ በመግለጫው ላይ ተጠቅሷል። አምነስቲ፤ እስሩን አስመልክቶ ባደረገው ጥናት በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች በክልሉ የተለያዩ ቦታዎች በሚገኙ አራት የእስር ካምፖች ውስጥ እንደሚገኙ እንደደረሰበት አስታውቋል። “ አምነስቲ ኢንተርናሽናል ባደረገው ጥናት፤ ግብረ ኃይሉ በመላው አማራ ክልል የሚገኙ አራት ጊዜያዊ የእስር ካምፖችን በሺዎች በሚቆጠሩ ሰላማዊ ሰዎች መሙላቱን አረጋግጧል ” ሲል በጥ