#ትህትና አንዱ #የስኬት #ጎዳና ነው።
#ትህትና አንዱ #የስኬት #ጎዳና ነው። "አቤቱ ንጹህ ልብ ፍጠርልኝ።" አሜን። #ምዕራፍ ፲፯ ትህትና ለራስም የውስጥ ሰላም የሚሰጥ ልዩ የፈጣሪ አምላካችን፤ የአላሃችን ልዩ ስጦታ ነው። የፈለገ የከበደ፤ የገዘፈ ፈተና ቢገጥም ትሁታዊ አቀራረብ ሻካራውን ግንኙነት ልጎ አንፃራዊ ልስላሴ የመፍጠር አቅም ይኖራዋል። አንዳንድ ጊዜ ሳታስቡት እልህ የገቡ ሰብዕናወች ይገጥማሉ። እናንተ የተበሳጩበትን ሁነት ላታውቁ ትችላላችሁ። ግን ግንኙነቱ ሳንክ እንደገጠመው ስትረዱ ምላሹን ግርጭርጭ መንፈስ ወደፊት ከማምጣት ይልቅ በትሁት መንፈስ ጉዳዩን ለማየት መፍቀድ ብዙ #የጎረቡ ጉዳዮች ፈውስ ሊሰጥ ይችላል። " ኃይል የእግዚአብሄር ነው።" ተስፋም ከእግዚአብሄር ዘንድ ነው። የተስፋ + የኃይል አቅም ትህትና ከታከለበት የስኬት ጎዳና ይጠረጋል። ይህን በስማበለው ሳይሆን እኔ በዘመኔ ያዬሁት የዕውነት ገጠመኝ ነው። የእናቴ የእብዬ ትህትና ይከብደኝ ሁሉ ነበር። የእሺታዋ መጠነ ሰፊ አቅምም ይከብደኝ ነበር። እኔ ከእሷ መሐጸን መገኜቴ ብቻ ሳይሆን እንደ ጓደኛም አብሮ አደጎች ነበርን። ብዙ በጣም ብዙ ነገሮችን ከእናቴ ወርሻለሁኝ። አባቴ አቨይም የዝምታ ዘውድ ነበር። ስለሆነም ተበድየም ይቅርታ እምጠይቀው እኔው ነኝ። ካሳ ካለም እምክሰው እኔው እራሴ ነኝ። ከሁሉ የሚያስደስተኝ ስጦታ #መስጠት ፤ ደስታን በገፍ ማቅረብ ሲሆን ክንዋኔውም በትህትና ነው። ይህም በመሆኑ ውስጤ የጸና ሰላም አለው። ቆፍጠን ማለትን በሚሹ የሥራ መስኮችም ቆፍጣና ነኝ። ሁልጊዜም በልኬ ነው መኖሬን መምራት እምሻው። እስር ቤትን አውቀዋለሁኝ። ስለዚህም እስር ቤት ያሉ ወገኖቼ ያሳስቡኛል። እስር ቤት እኮ #የ...