#ደስታን መጥኖ ስለማስተዳደር። እዮራዊ ምርቃት እንዳይነሳ።
#ደስታን መጥኖ ስለማስተዳደር። እዮራዊ ምርቃት እንዳይነሳ። "አቤቱ ንጹህ ልብ ፍጠርልኝ፤ ቀናውን መንፈስ በውስጤ አድስ።" አሜን። (መዝሙር ፶፩ ቁጥር ፲) #ምዕራፍ ፳። (20) ተመስገን። #ለውዶቼ ለአዱኛወቼ ትሁታዊ ጤና ይስጥልኝ። ለማህበረ - ቅንነት፤ ለቤተ - ሥርጉትሻ ውዶች ህሊናዊ ክብር እና ትሁታዊ ሰላምታ እንሆ። እንዴት አላችሁልኝ። የምር ንፍቅቅ ብላችሁኛል። የዕውነት የውስጤ ውስጥ መሆናችሁ የሚገለጥልኝ እንዲህ ሳላያችሁ ስስነብት ነው። ስንብቾው እንዴት ነው። እንቁጢ እንዴት አለፈች? በመስከረም በርካታ ወገኖቻችን ልዩ የበዓል ሴሪሞኒ አላቸው። በዚህ አጋጣሚ እንኳን አደረሳችሁ። በዘርፋ ደካማ ነኝና፤ ሳላስታውስ ስቀር እለፋኙ። በተረፈ 2019 ሰላም በእያንዳንዳችን ቤት የሚገባበት ያድርግልን። አሜን። 1) #ደስታና ሐሤት ምን እና ምን ናቸው በሥርጉዬ - ፍልስፍና። 1.1) ደስታ ምድራዊ፤ ሰው ሠራሽ፤ ጊዜያዊ እና ቆይታውም የማይታመን፤ ትነት ሊገጥመው የሚችል። 2.2) ሐሤት ሰማያዊ እና አማኑኤል ሠራሽ ገኃዱ ዓለምንና መንፈሳዊውን ዓለም የሚያገናኝ ቋሚ እና ዘላቂ ድልድይ። የምድራዊውን ደስታ በሚመለከት የመጀመሪያ ጹሁፌ የመቀሌ በመከላከያ ሥር ገባች ርችት፤ ፈንጠዝያ፤ ፌስታ ጊዜ ነበር የፃፍኩት። ከዛም በኋላ በተለያዬ ጊዜ የተንጠራራ የፌስተ ድለቃ ሳስተውል በልክ ያዙት በማለት ማሳሰቢዬ አልቀረም። 2) #ለምን ? 2.1) ባለ ደስታው ተጨማሪ ደስታ ሲያገኝ #መደርደሪያ እንዳያጣ፤ ማስቀመጫው፤ እንዳይጠበው። 2.1) ባለ ደስታው ደስታው እየራቀው ሲሄድ ተስፋ ቆራጭ ሆኖ ለሥነ - ልቦና #ህመም እንዳይዳረግ። 2....