ጉበትዎ እንደተጎዳ የሚነግሩዎት 10 ምልክቶች
ጉበትዎ እንደተጎዳ የሚነግሩዎት 10 ምልክቶች ጉበት በአካላችን ትልቁ ኬሚካል አመንጪ አካል ነው። ጥቅሞቹ ብዙ ናቸው። 3 ዋና ጥቅሞች አሉት። ባይል የሚባል ምግብን ለመፍጨት የሚያግዝ አረንጓዴ ኬሚካል ያመነጫል። በሰውነታችን ያሉ መርዛማ ንጥረ ነገሮችን ያጸዳል። የሰውነታችንን ሃይል ፍላጎት ላማሟላት ግሉኮስ ያመነጫል። ከጉበት አስፈላጊ ጥቅሞች አንጻር ጤናውን መከታተል ለሰውነታችን ጤና አስፈልጊ ነው። ጥሩ አመጋገብ፣ አካል ብቃት እንቅስቅሴ እና በቂ እንቅልፍ ማግኘት ለጉበት ጤና አስፈላጊ ነገሮች ናቸው። አልኮል እና ቡና ማብዛት የጉበታችንን ጤና አደጋ ላይ ይጥሉታል። ጉበታችን ሲታመም ህመሙ በብዙ ሰውነት አካላታችን ላይ ይንጸባረቃል። የተለያዩ የጉበት በሽታዎች አሉ። የተለመዱት ሲሮሲስ፣ ሲስቲክ ህመም፣ የጉበት ፋቲ ህመም፣ የሃሞት ጠጠር እና ሄፕታይተስ ናቸው። ጉበትዎን ሁሌ የሚንከባከቡ ከሆነ ጤናዎ ላይ ለውጡን ያዩታል። የጉበት ጉዳት ካለዎ አስቀድሞ በመታከም የመዳን እድልዎን ያሰፋሉ። የጉበት ጉዳት ምልክቶች 1) ማቅለሽለሽ እና ማስመለስ derneuemann / Pixabay ብዙ ሰው የማቅለሽለሽ ስሜት እና ማስመለስን እንደ አደገኛ የበሽታ ምልክት አይቆጥራቸውም። ያለምንም ምክንያት የማቅለሽለሽ ስሜት ወይም ማስመለስ ካጋጠመዎ የእኩላሊት ወይም የጉበት ህመም ያመላክታል። ስሜቱ የተሰማዎ ግን በምግብ መመረዝ ወይንም በሌላ የተያያዘ ህመም ከሆነ የጉበት ጉዳት የመሆን እድሉ ትንሽ ነው። የጉበት ጉዳት ያጋጠማቸው ሰዎች የማይለቅ የማቅለሽለሽ ስሜት ይሰማቸዋል። ይህ ስሜት የሚመጣው የጉበታችን መርዛማ ንጥረ ነገሮችን የማስወገድ ሃይል ስለተዳከመ ነው። የምግብ አፈጫጭ ለውጥም ማቅለሽለሽ እና ማስመለስ ያስከትላል። በየግዜው የማቅለሽለሽ እና የማስታወክ ስሜት ጤናችንን በከፍተ...