ልጥፎች

ከኦክቶበር 30, 2023 ልጥፎች በማሳየት ላይ

ግሥ የሌለው መሪነት አልቦሽነት።

ግሥ የሌለው መሪነት አልቦሽነት። "ከንቱ የከንቱ ከንቱ ሁሉም ነገር ከንቱ።" ጠቅላይ ሚር አብይ አህመድ #ማሰሪያ #አንቀጽ የላቸውም። የድርጊቱ መነሻም መዳረሻውም ከኦዲዬንሱ ውጪ ነው። አሁን አሁን ሳስበው መሪነት ጽንሰ ሃሳቡ የገባቸው አይመስለኝም። በሌላ በኩል #የመሪነት #ስሜቱንም የተረዱት አይመስለኝም። በተጨማሪነት የመሪነት #መነሻውን ያወቁትም አይመስለኝይ። ይህም ብቻ አይደለም #የመሪነት #ቅደም ተከተሉንም የተረዱት አይመስለኝም። እርግጥ እሳቸው ያቀዱትን እዬከወኑ መሆኑን አያለሁኝ። ያ ማለት ግን የአገር መሪነቱን ሚና እዬተወጡ ነው ማለት አይደለም። መሪነት ለእሳቸው 365 ቀን መናገር፤ ለሳቸው ደስ የሚላቸውን ፕሮጀክት የድሎት አቅዶ መፈፀም፤ አስደሳች እና አዝናኝ የሆኑ ጉዳዮችን ነጥሎ ትኩረት መስጠት መሪነት መስሏቸዋል። በፍፁም የመሪነትን #ስሜቱን አልተረዱትም። በፍፁም። መጓዝ፤ ንግግር ማድረግ፤ ድንገተኛ ክንውኖች ላይ አቅምን ማፍሰስ መሪነት መስሏቸዋል። የሠፈር መሪ አይደሉም። የዓለም የሰላም አባት የሚመራውን አገር ቀጠናውን በሰላም ማስተዳደር የተሳነው፤ እወክለዋለሁ በሚለው ኦሮምያ ክልል እንኳን ከህዝቡ ጋር የተቆራረጠ። ከበሻሻ በስተቀር በዬትኛውም ሁኔታ የወጡበት ማህበረሰብ ውክላዊ ፖለቲካዊ ሂደት አብሰንት የሆኑ። የሚገርመኝ እሳቸው ከተደሰቱ፤ እሳቸው ከደለቁ ከ110 ሚሊዮን ህዝብ በላይ የሆነው የኢትዮጵያ ህዝብ ስሜቱ ምን ይሁን ምን ጉዳያቸው አይደለም። እረፍት አልባ የሚታትሩት ለራሳቸው ፍስኃ ስለመሆኑ ነው እኔ እማስተውለው። ህዝቡ ሲከፋው አይከፋም። ሲያዝን አያዝኑም። ሲራብ አይራቡም። ሲያለቅስ አያለቅሱም። ለእኔ የቤተ መንግሥቱ #ሃውልት ወይንም ማስዋቢያ ዲኮሬሽን ሆነው ነው የሚታዩኝ። ኦሮሞ ጠቅላይ ሚር ሆነ።

ከአሰር አቮል አይመጣም፤ ከሻገታም ትኩስ እንጀራ አይታለምም እናም አይስጉ።

  ከአሰር አቮል አይመጣም፤ ከሻገታም ትኩስ እንጀራ አይታለምም እናም አይስጉ።      "ህግ ተላላፊወችን ጠላሁ።" እጅግ በተደጋጋሚ ጊዜ ጠቅላይ ሚር አብይ አህመድ ከዛው ከሻገተው የኢህዴግ መንፈስ አዲስ ኃይል ወጥቶ ይፈነቅለኛል ብለው ይሰጋሉ። መንገዱን እናውቀዋለን አትሞክሩት ሲሉ አዳምጣለሁኝ። በዚህ ቅዠት እነ ቲም አንባቸው ተመነጠሩ። የአማራ ልጆች ተጋዙ፤ ተሰወሩ፤ ታገቱ፤ ተረሸኑ፤ ተሳደዱ። ሁልጊዜ የሚያባንናቸው መፈንቅለ መንግሥት ከዛው ከዛገው ብርታቸው ውስጥ ነው። እኔ ደግሞ እላለሁ። አይስጉ። ከሽውራር የምንጠብቀው ትፍስህት የለም። ቢሞከርም ይጨነግፋል። ምክንያት ኤክስፓዬርድ ያደረገ ስለሆነ። በጣም በተደጋጋሚ በእናንተ ጥረት ብቻ ለውጥ እንደመጣ ያስባሉ። ዕሳቤው ልሙጥ ነው። ከዛ የበሰበሰ አካል ቀጣይ አካል እንዲቀጥል የተደረገው የእኛ የወል ስምምነት ስለነበረ ብቻ ነው። ኢትዮጵያዊነት ሱሴ ነው የሠራው ደባ ነው እንጂ ኢህዴግ ታምኖ በዓለም ዓቀፍ ማህበረሰቡ ይሁንታ ያገኛል ተብሎ አይታሰብም። ጠቅላይ ሚር አብይ ስላልነበሩበት ያልገባቸው ሚስጢር ይህ ነው። ሁለተኛ የሚጭበረበር የለም። ፈፅሞ። እናማ ተፈነቃቅላችሁ ኃይል ነን ብሎ የሚከሰት ማንም ይሁን ማን የሚመጣ አካል ተቀባይነት የለውም። ኢትዮጵያ ሙሉ 60 ዓመት ረግረግ የወደቀችበት የመከራ ሥረ መሠረትን የሚነቅል ሂደት ነው እኔ በግሌ የምሻው። ያ ደግሞ ሥር ነቀል ለውጥ በአዲስ ኃይል እና ተፈጥሯዊነት መንፈስ። ትራፊም፤ ቅርጥምጣሚም አያሰኜንም። በሌላውም በኩል ህልም ሊኖር ይችላል። ያም አይሆንም። ከግንቦት 7 በላይ ሚሊዮኖችን መንፈስ የተቆጣጠረ አልነበረም። ቻለ? አልቻለም። የህወሃት መሸኜት ለሁሉም ዱብ ዕዳ ነበር። ሥራ ይጠይቃል። ለዚህም ነው ሲግለበለብም፤ ሲፈላም፤ ሲንተከተክም በጥሞ